ክብርት ፕሬዚዳንት አምባሳደር ሣህለ-ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ፊት ቀርበው ካደረጉት ንግግር የተወሰደ:-

“ታላቅ አገር የመገንባት ህልማችንን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ምንም አቋራጭም ሆነ አማራጭ የለንም፡፡

ስለዚህ ሁላችንም ሰላማችንን አጥብቀን እንድንጠብቅ ከሁሉ በላይ ሰላም ሲታወክ በምትሰቃየዋ በእናት ስም አጥብቄ እጠይቃችኋለሁ፡፡

· ሰላም ከራሳችን ጋር፣

· ሰላም በቤተሰብ፣

· ሰላም ከጎረቤታችን ጋር፣

· ሰላም በመንደራችን፣

· ሰላም በወረዳዎች መካከል፣

· ሰላም በክልሎች መካከል፣

· ሰላም ከጎረቤት አገሮች ጋር

· ሰላም በዳያስፖራ፣

· ሰላም፤ ሰላም፤ ሰላም እላለሁ እጅግ ከጠበቀ አደራ ጋር፡፡

ኢትዮጵያዊነትን ከሰለማዊነት ጋር አንድና ያው ለማድረግ በጋራ እንስራ፤

በሰላም እጦት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች በመሆናችን በዚህ የኃላፊነት ቆይታዬ ዋነኛው ትኩረቴ መላ የኢትዮጵያን ሴቶችና ሰላም ወዳድ ወንዶችን እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ሰላም ወዳድ የሆኑትን ሁሉ ከጎናችን በማሰለፍ ሰላም በማስፈን ላይ እንድንረባረብ ማድረግ ይሆናል፡፡

የተከበሩት ምክር ቤቶች እና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎኔ እንደምትሰለፉ እተማመናለሁ፡፡”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here