በመጀመሪያዎቹ የህፃንነት ጥቂት ወራት ለአእምሮአቸው እድገት የሚጠቅሙ ምግቦች በማዘጋጀት መመገብ ለህፃናት ጤንነት መጠበቅ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ።

የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚም የህፃናት ጤናማ የአንጎል እድገት እንዲረጋገጥ በመጀመሪያቸው 1 ሺህ ቀናት የሚያስፈልጉ ምግቦች ዝርዝርን አውጥቷል።

የሕክምና አካዳሚው ኮሚቴ ባሳተመው መፅሄት መሠረት፥ ፕሮቲን፣ ዚንክ፣ የተወሰኑ ቫይታሚኖች እና ከቅባት እህሎች እና ዓሳ የሚገኝ ፋቲ አሲድ ለጤናማ የህፃናት የአእምሮ እድገት ወሳኝ ናቸው።

ጥናቱ የእነዚህን ንጥረ ነገሮች እጥረት ያለባቸው ምግቦች በአእምሮ እድገት ውስጥ የዕድሜ ልክ ችግር እንዲፈጠር ሊያደርጉ ይችላሉ ነው የሚለው።

በሚኒሶታ ማሶኒክ የልጆች ሆስፒታል እና የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶክተር ሳራህ ጃኔ፥ ህፃናት የእናት ጡት ወተት እስከ ስድስት ወር ዕድሜያቸው ድረስ እንዲጠቡ ይመክራሉ።

አትክልት.jpg

ከዚያ በኋላ የእናት ጡት ወተት ህፃናቱን ለአእምሮአቸው እድገት የሚጠቅመው የአይረን እና የዚንክ ንጥረ ነገሮች መጠን አሟልቶ የያዘ አይደለም ይላሉ።

ስለዚህ እናቶች ከጡት ወተት በተጨማሪ ለህፃናቱ በተጠቀሱት ንጥረ ነገሮቹ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ አለባቸው ሲሉ ባለሙያው ያብራራሉ።

በዚህም ህፃናቱ ከእናት ጡት ቀጥሎ በስጋ የበለፀጉ ገንቢ ምግቦች፣ ፍራፍሬዎች፣ የቫይታሚን እና ማእድን ይዘት ያላቸው አትክልቶችን ቢመገቡ ጥሩ መሆኑም ተጠቁሟል።

ባለሙያዋ እንደሚሉት ህፃናት በመጀመርያዎቹ ወራት ለአልሚ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው።

በዚህም አእምሯቸው ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ በፍጥነት የሚያድግበት ስለሆነ ወላጆች ይህ የጊዜ እንዳያመልጣቸው ነው የመከሩት።

ምንጭ፦ www.health.com

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here