ውድድሩ በሀገር አቀፍ እና በክልል ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን ከ30 በላይ ሴት አምባሳደሮች ይመረጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ዓላማውም የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ንቅናቄን ለማጠናከር መሆኑን የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ገልጿል።

ተመራጭ አምባሳደሮችም ለግድቡ ገፅታ ግንባታ የሚሰሩ ሲሆን፥ ህዝባዊ አነቃቂ ንግግሮችን የማድረግ ሚና አላቸው ተብሏል።

በሁሉም ክልልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሚደረገው ምርጫ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከወጡት መካከል በሀገር ደረጃ አንድ ሴት አምባሳደር እንደምትመረጥ ነው ፅህፈት ቤቱ የጠቆመው።

ቀሪዎቹ ክልሎቻቸውን ወይም ከተማ አስተዳደራቸውን ይወክላሉ።

የጽህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ እንድሉት፥ ውድድሩ በክልሎች ጥር 30 ቀን 2010 ዓ.ም፥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ መጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

አምባሳደሮቹ የግድቡ የመሰረተ ድንጋይ የተቀመጠበት 7ኛ ዓመት በመጪው መጋቢት በጉባ በሚከበርበት ዕለት ለህዝብ ይፋ ይሆናሉ ነው ያሉት።

በግድቡ ዙሪያ ዕውቀት ያላት ማንኛዋም ኢትዮጵያዊት በአምባሳደርነት ውድድሩ መሳተፍ እንደምትችልም አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here