ቲም ለማ የዛሬ ዓመት ለዲሞክራሲና ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ ከጀመረ ወዲህ ሀገራችን በታሪኳ አይታው የማታውቀው ግጭትና መፈናቀል ገጥሟታል።

ከአንድ ጓደኛዬ ጋር የሰበሰብነው ዳታ እንደሚያሳየው ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በ45 ቦታዎች ግጭቶች ተከስተዋል።

ከነዚህ መካከል 20 በሚሆኑት ላይ የህዝብ መፈናቀል ተከስቷል። ይህ ድምር በ26 ዓመታት የታዩትን ግጭቶች ግማሽ ያህል ይሆናል።

እነዚህ ክፉ ድርጊቶች በዘፈቀደ የተከሰቱ አይደሉም። ከነዚህ ክፉ ድርጊቶች ጀርባ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጎ የማይመኙ ማጅራት መቺዎች እንዳሉ ግልጽ ነው።
—-
የግጭቶቹ እና መፈናቀሎቹ ዓላማ በሁለት ደረጃዎች ሊታይ ይችላል።

# ከመጋቢት 2010 በፊት ማጅራት መቺዎቹ ግጭቶቹን የሚለኩሱት ቲም ለማ ወደ ስልጣን እንዳይመጣ ለመከላከል እና ለነፃነት የሚያደርገውን ትግል በእንጭጩ ለማስቀረት ነው።

# ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመጋቢት ወር መራሔ መንግስት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ደግሞ የማጅራት መቺዎቹ ዓላማ ለአዲሱ መንግስት መጥፎ ገጽታ ማሰጠት፣

በትግል አጋሮቹ መካከል መከፋፈልን መፍጠር፣ መንግስት ትኩረቱን በግጭቶቹ ላይ ብቻ እንዲያደርግ ግፊት መፍጠር፣ ህዝቡ በዶ/ር ዐቢይ መንግስት ተማርሮ ለአመጽ እንዲነሳሳ መገፋፋት እና መንግስትም ተስፋ ቆርጦ ስልጣኑን እንዲያስረክብ ማድረግ ነው።
—-
ታዲያ የዶ/ር ዐቢይ መንግስት በማጅራት መቺዎቹ ግፊት ስልጣን ቢለቅ በእርሱ ቦታ የሚመጣው መንግስት ለእኛ የሚሆን ነው? በፍፁም!!

የማጅራት መቺዎቹ ምኞት ሀገራችን አይታው በማታውቀው አፈና ውስጥ የሚከታትን አፋኝ ስርዓት መመሥረት ነው። ስለሆነም ነው በየጊዜው “ንቁ! ተሳሰቡ” የሚል መልእክቴን የማስተላልፈው።
—-
ማጅራት መቺው ቡድን በየጊዜው ግጭት የሚቆሰቁሰው ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን እንደ ድክመት በመቁጠር ነው። ዓላማውና ፍላጎቱ እንዳይሳካለት ካሻን እጅ ለእጅ ተያይዘን መቆም አለብን።
—-
ስለዚህ ወዳጆች!
ተቻቻሉ!
አንድ ሁኑ!
እጅ ለእጅ ተያያዙ!

ልዩነታችንን በጉያችን ይዘን ባርነትን በሚመኙልን ጠላቶቻችን ላይ በሩን እንጠርቅምባቸው።

ሁላችንም ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጎን እንቁም!!
—-
ሼር፣ ሼር፣

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here