Yared Shumete – ያሬድ ሹመቴ … እንዲህ አለ

ፖሊስ በተሳሳተ መረጃ እና በግብታዊነት በተለያዩ ቦታዎች ንፁኃንን እያሰረ ስለመሆኑ በቂ መረጃ ያለኝ ብቻ ሳይሆን እኔም የዚህ ድርጊት ሰለባ ሆኛለሁ።

እርዳታ ከሚያስተባብሩ ወጣቶች መሀል አንዱ የፖሊስን አዛዥ ፎቶ አንስተሀል በሚል ክስ ያስተባበርከው አንተ ነህ ተብዬ ለ 5 ሰዓታት ያህል ታስሬ ተፈትቻለሁ።

ይህንን እውነት ቃሌን የተቀበለውን የላዛሪስት ጉለሌ ፖሊስ መምሪያን ጠይቆ ማረጋገጥ ይቻላል።

የመንግስትን የአሸባሪነት ተግባር በድጋሚ የጀመራችሁ በአስቸኳይ አቁሙ።

ዶ/ር ዐብይ “አጣርተን እናስራለን እንጂ አስረን አናጣራም” ያልከን ለሙስና ወንጀለኞች ብቻ ነው እንዴ?

ሠላም ለኢትዮጵያ
ማስተዋል ለመሪዎች ይስጥልን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here