በ1936 የNazi አመታዊ ስብሰባ ላይ ወፊት በተቀሰሩ ሺ ቀኝ እጆች መሀል ያልተዘረጋ የአንድ ሰው ብቸኛ እጅ ታየ- የኦገስት ላንዲሜሰር!

በወቅቱ ገናና ከነበረው የሀገሩ ገዢ ፓርቲ ጋራ ለአራት ዓመት የዘለቀው ኦገስት ላንድሜሰር (August Landmesser) ቀደም ሲል የቀኝ እጁን ወደፊት እየዘረጋ እጅ ይነሳ የነበረው የ Hitler ወዳጅ:

የናዚ ቅን አገልጋይ ንፁሁ ጀርመናዊው 🇩🇪 ኦገስት ላንድሜሰር ( August Lansmesser) ቀስ በቀስ ሀገሩ እየሄደችበት ያለው የግፍ ጎዳና እየጎረበጠው መጣና ለማበር ተቸገረ::

በ1936ማ ጨርሶ አልሆነለትም! እምቢ አለ!

ድንገት ሰው አፈቀረና – ሀገሩን እስከመሪዋ ካዳት!

ኦገስት ከተከለከለው ዘር ከአይሁድ ሴት ጋር ክፉኛ ተዋደደ::

* ሀገሩ ጀርመን ከምትጠየፈው:

* ገዢው ፓርቲ እንደከብት ጥርስ አፍንጫውን እያየ ከሚያስረው:

* ሊጨፈጨፍ ከተጋዘ ህዝብ:

* እንደ ነፍሳት የምርምር መሞከሪያ ሊያደርገው ካጎረው ጠያፍ ዘር የተወለደች አሁዳዊት ሴት ማረከችው::

ይህም ለጀርመናዊያኑ እና ለናዚያውያን ክብረ-ነክ ሆኖ ተገኘና

“ዘርን በማራከስ- ከተጠላ ህዝብ ጋር በመጣመር” በሚል ኦገስት ተከሰሰ::

የሚወዳት ሀገሩ የተወለደባት እና የሚመካባት ጀርመን ከአረመኔነት ጥግ ስትደርስ እርሱም ለእውነት ጨከነ::

የወደዳትን አይሁዳዊት አገባት- አከበራት

ይሄም ዓለም ለታሪክ የሚዘክረው ፎቶ  በካሜራ ማስታወሻ ለምስክርነት ተመዘገበ::

6 ሚሊዮን አይሁዳዊያንን ካጠፉ ክንዶች ጋር ያልተባበረ እጅ:

የክፋትን ሀያላን ብቻውን የተገዳደረ የኦገስት ያልተዘረጋ እጅ መልዕክት ይህ ነው :-

* የአንድን ዘር የበላይነት አልቀበልም እምቢ!

* የሰው ልጅ በማንነቱ ምክንያት የሚደርስበትን እንግልት አልደግፍም እምቢ!

* ለዘር ጭፍጨፋ እምቢ!

* ለጭካኔ እምቢ ! (እስከነሚስቱ ህይወቱን እስኪከፍልበት ድረስ)

እርግጥ ነው :- ሰው ከሀገር : ከመሪ: ከፓለታካ አቋም ይበልጣል!

*እውነት ደሞ የነፍስን ዋጋ ያክላል::

ወገኔ እንዳታለል ለዘረኝነት እምቢ በል!

ተለይ! ተለይ! ተለይ!

ብሩህ ቀን BIRUH QEN

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here