አርቲስት #ደበሽ_ተመስገን ወደትወና የገባው ትምህርቱን ከ9ኛ ክፍል አቋርጦ ነበር።

በወቅቱ በተለያዩ ቲያትሮችና ቲቪ ድራማዎች ላይ ሲተውን በአጭር ግዜ እውቅናን አገኘ።

ታዋቂ ሆኖም ግን ሁልጊዜ አንድ ነገር ያስጨንቀው ነበር።

ደበሽ በ #etv መዝናኛ እንዲህ አለ።

“አንድ ቀን ሚስት ሳገባና ልጆች ስወልድ ልጆቼን ምን እላቸዋለሁ ብዬ እጨነቅ ነበር።

እኔ ሳልማር እየሰራሁ እነሱን ምን ብዬ ስለትምህርት ጥቅም እመክራለሁ ስል አስብ ነበር።

ከዚያም ለመማር ወስኜ የማታ ገባሁ። የቀን ተሪማዎች ሲለቀቁ እኔ ደብተሬን ይዤ እደርሳለሁ። ምንም ሳልሳቀቅ ወደውስጥ እዘልቃለሁ።

አንዳንዶች በአትኩሮት ሲያዩኝ ሰላምታ እየሰጠሁ አልፋለሁ።

ለመጀመሪያ ግዜ ክፍል ውስጥ ገብቼ ፊትለፊት ተቀመጥኩ። መምህሩ እንዳየኝ ‘እዚህ ክፍል ነህ?’ አለኝ።

‘አዎ’ አልኩት።

‘ልትማር ነው?’ አለኝ ‘አዎ’ አልኩት።

ትንሽ ቆየና ‘ደበሽ አይደለህም እንዴ’ ሲል ጠየቀኝ። ‘አዎ’ ነኝ አልኩት።

ብዙ ግዜ ታዋቂ ሆኖ መማር ያስቸግራል። እኔ ግን ዓላማ ስለነበረኝ ተወጥቼዋለሁ።

ከጀመርኩ ወዲያ ሳላቋርጥ ለ15 ዓመታት ተምሬያለሁ።

አሁን ለሶስት ሴት ልጆቼ በማስተርስ ዲግሪ ስመረቅ የተነሳሁትን ፎቶ ከግድግዳው ላይ እያሳየው ‘ልጆቼ በርትታችሁ ተማሩ የማወርሳችሁ ኃብት ትምህርት ብቻ ነው!’ እላቸዋለሁ።”

#ለትምህርት_አይረፍድም

Betelhem Tesfaye

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here