መንግስት ለማንነት ጥያቄዎች አስኳይ መፍትሄ እንዲሰጥ በሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የማንነት ጥያቄ በሚያቀርቡ ንጹሀን ወገኖች ላይ የሚወሰደውን የኃይል እርምጃ፣ግድያ እና እስራት አውግዘዋል፡፡

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት እና የጣና ሀይቅንም ካጋጠማቸው አደጋ መንግስት በአስቸኳይ ሊታደጋቸው ይገባል ነው ያሉት፡፡

በሰልፉ ላይ የተገኙት የመርሳ ከተማ ከንቲባ አብዱ እንድሪስ የራያ እና የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ በህገ-መንግሥታዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲፈታ ከህዝቡ ጎን በመሆን ጥረት እንደሚያደርጉ ነው የተናገሩት፡፡

በዕለቱም ከራያ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ6 ሺህ 8 መቶ ብር በላይ ተሰብስቦ ለራያ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ መሰጠቱን ከሀብሩ ወረዳ የመ.ኮ.ጉ.ጽ.ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

(አብመድ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here