ሜሱት ኦዚል በደረሰበት የዘረኝነት ጥቃት እና የሚገባውን ያህል ክብር ስላልተሰጠው ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን አሳወቀ፡፡
የዘር ሀረጉ ከቱርክ የሚመዘዘው የመድፈኞቹ ተጨዋች በተደጋጋሚ በተነሳሽነት አይጫወትም በመባል ይተቻል ፤
1.6 ሚሊዮን ስደተኞች ባሏት ጀርመን ውስጥ በአንድ ወቅት ሲነሳ ስለነበረው ዘረኝነትም በጥብቅ ተሳታፊ ነበር ፡፡
2014 ላይ የአለም ዋንጫ ክብርን ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ያገኘው ኦዚል ከ2011 አንስቶ በደጋፊዎች ምርጫ አምስት ጊዜ የአመቱ ምርጥ ጀርመናዊ ተጨዋች ተብሎም ተሸልሟል ፡፡
ከወራት በፊት ከቱርኩ ፕሬዝደንት ሬሲብ ጣዒብ ኤርዶሃን ጋር ፎቶ ከተነሳ በኃላ ግን በርካታ ትችቶችን ማስተናገድ ጀመረ፡፡
ከሌላኛው በዘር ቱርካዊ በዜግነት ጀርመናዊ ኤካን ጉንዶጋን ጋር በመሆን ነበር ከፕሬዝዳንቱ ጋር ፎቶውን የተነሱት ፤
በዚህም የተነሳ በሩሲያው የአለም ዋንጫ በማማሟቅ ላይ እያሉ በአንዳንድ ደጋፊዎች ስድብ ደርሶባቸዋል ፡፡
ጀርመን ከ80 አመት በኃላ በአለም ዋንጫ ከምድብ ማለፍ ሲሳናት ኦዚል በቡድኑ ውስጥ ስኬታማ ካልሆኑ ተጨዋቾች አንዱ ሆኗል፡፡
የጀርመን እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ሬይናርድ ግሪንደልም ከውድድሩ በኃላ ኦዚልን ባሳየው አቋም ተችተውታል
እሱም በቲውተር ገፁ “በግሪንደል እና በደጋፊዎቹ አይን ስናሸንፍ ጀርመናዊ ነኝ ስንሸነፍ ደግሞ ስደተኛ ነኝ” በማለት ቲውት አድርጓል ፡፡
አክሎም ታክስ ከፋዩ ቢሆንም ፣ በጀርመን ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች እርዳታ ቢያደርግም
በተጨማሪም ብራዚል ላይ የአለም ዋንጫውን ሲያነሱ የቡድኑ አባል ቢሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን እንደዛ እንደማይታሰብ ተናግሯል ፡፡
“ከባድ ቢሆንም በደንብ ካሰብኩበት በኃላ በቅርቡ በተከሰቱት ሁነቶች ምክንያት ከጀርመን ብሄራዊ ቡድን ጋር መቀጠል እንደሌለብኝ ወስኛለሁ ይህንን ያደረጉት በደረሰብኝ የዘረኝነት ጥቃት እና ክብር ማጣት ነው፡፡
የጀርመን ብሄራዊ ቡድንን ማሊያ ከዚህ በፊት በኩራት እና በደስታ ለብሻለሁ አሁን ግን አይደለም ፡፡
ከ2009 ጀምሮ ብዙ ነገር ብሰራም ያለ መፈለግ ስሜት ተሰምቶኛል ፡፡” ብሏል፡፡

ኦዚል 92 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን 23 ግቦችን አስቆጥሯል ፡፡

Jimi Jelaledin

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here