የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ፍጹም አረጋ ከነገ ጀምሮ በኢንቨስትመንት ኮሚሽነርነት እንደሚቀጥሉ ገልጸው ምትካቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳን አስተዋውቀዋል።

በስራቸው በአዲስ መልክ የተቋቋመው ፕሬስ ሴክሬታሪያትም የመረጃ ፍሰቱን ቀጣይነት ባለውና በተደራጀ መልኩ ለማከናወን እንደሚያስችልም ተናግረዋል

አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስም ፕሬስ ስክሬቴሪዋን ቢልለኔ ስዩምን ባስተዋወቁበት አጭር የመግቢያ ንግግራቸው ለህበረሰተሰቡ ተገቢውን መረጃ በወቅቱና በተተቀናጀ መልኩ ለማዳረስ ሴክሬቴሪያቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

የቀድሞው የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋና አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ አብዲሳ

” ምንም ከህዝብ የሚደበቅ ነገር አይኖርም ፤ ካሁን በኋላ ከሚዲያ ተቋማት ጋር እንደአንድ ቤተሰብ ተባብረን አንሰራለን ብለዋል አቶ ሽመልስ ።

የፕሬስ ሴክሬታሪዋ ቢልለኔ ስዩም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት መግለጫቸው ሴክሬቴሪያቱ በመንግስት ውሳኔዎችና አቋሞች ዙሪያ ወቅታዊ፤ ግልጽና ትክክለኛ መረጃ የመሰብሰብና የማሰራጨት ኃላፊነት አንደተሰጠው ተናግረዋል።

በመንግሥት አሰራር ላይ የሚነሱ የህዝብ ምላሾች፤ አስተያየትና ግብረመልሶቸን የማቀናጀት፣ የመተንተንና የማሳደግ ስራም ይጠብቀዋል።

ለተሻለ ግልጽነት ያለው ዘገባ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና በመገናኛ ብዙሃን መካከል ያለውን ግንኙነት የማጠናከር ተግባርም ለሴክሬቴሪያቱ የተሰጠ ኃላፊነት እንደሚሆን ነው የገለጹት።

የቀድሞው የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋና የፕሬስ ሴክሬታሪዋ ቢልለኔ ስዩም

በቅርቡም የሴክሬቴሪያቱን ዝርዝር አወቃቀር፤ ኃላፊነትና የመረጃ ፍሰት በተመለከተ መግለጫ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል።

ፕሬስ ሴክሬቴሪዋ በቀላሉ ለመረዳት በሚያስችል መልኩ ለህዝብ ቅጂ በማቅረብ ገንቢ ግብዓቶችን በመውሰድ ትግበራዎችን የማስተካከል ዓላማ ስላለው የመንግሥት ባለአንድ ገጽ የዕቅድ ሰሌዳም አብራርተዋል።

ባለአንዱ ገጽ የዕቅድ ሰሌዳ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችን የሥራ አፈጻጸምና የሚመለከታቸውን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

“ተገቢውን መረጃ በወቅቱ ለህዝብ እናደርሳለን” አዲሷ ፕሬስ ስክሬቴሪ ቢልለኔ ስዩም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here