መቼስ በዚህ ወቅት ጫኑኝ የማይል የስልክ መተግበሪያ የለም። ዓለም ራሷ የስልክ መተግበሪያዎች ውስጥ ተከናንባ እየገባች ይመስላል።

የደም ግፊት መጠንን ከሚለኩት ጀምሮ ቋንቋ መማሪያዎች፣ ቀን መቁጠሪያዎች፣ ቁርስ ምሳ ማዘዣዎች፣ ታክሲ መጥሪያዎች፣ ባንክ ሂሳብ ማንቀሳቀሻዎች፤ ብቻ የሌለ ዓይነት የስልክ መተግበሪያ የለም።

ፈተናው ሐሰተኛውን ከእውነተኛው መለየት ነው። በዚህ በኩል እኛ እንርዳዎት! የሚከተሉት ሦስት የስልክ መተግበሪያዎችን ጫኑ ማለት መከራን ስልክዎ ላይ ጫኑ እንደማለት ነው።

ስልክዎን ለጤና መቃወስ የሚያጋልጡ ሐሰተኛ መተግበሪያዎች (Apps) የሚከተሉት ናቸው።

የሞባይል ባትሪ ዝቅተኛ መሆኑን የሚያሳይImage copyrightGETTY IMAGES

1.የባትሪ ዕድሜን እናራዝማለን የሚሉ

የሞባይል ባትሪ እንደ ቋንቋ ነው፤ ይወለዳል፣ ያድጋል ይሞታል። ልዩነቱ በምን ፍጥነት ይሞታል የሚለው ነው። በዚህ ረገድ የባትሪው ኦሪጅናልነትና የአገልግሎት ዘመን ቁልፍ ጉዳይ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ባትሪ ቶሎ እየሞተ ሲያስቸግር ያነጫንጫል። በዚህ ጊዜ የባትሪዎን ዕድሜ ላራዝምልዎ የሚል መተግበሪያ ሲመጣ ያጓጓል። ጫኑኝ ጫኑኝ ይላል። አይቸኩሉ!

የቴክኖሎጂ ጋዜጠኛ የሆነው ኤሪክ ሄርማን “የባትሪ ዕድሜን የሚያቆይ ምንም ዓይነት መተግበሪያ የለም” ይላል።

ይልቅ የባትሪ ዕድሜን ለማራዘም መፍትሄው ብዙ ዳታ የሚያሟጥጡ መተግበሪያዎችን ለጊዜው ዝም ማሰኘት ነው። እምብዛምም የማያስፈልጉ መተግበሪያዎች ከጀርባ ሆነው ባትሪን ይመዘምዛሉ። የ

ስልክዎ የብርሃን ድምቀት፣ የኢንተርኔት ዳታ፣ የዋይ ፋይ ማብሪያ ማጥፊያ ባትሪን ይመገባሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስልክዎን “ናይት ሞድ” ወይም “ባትሪ ቆጥብ” የሚለው ማዘዣ ላይ ያድርጉት።

ሌላው መፍትሄ ባትሪ ኮንፊገሬሽን ላይ ገብቶ የባትሪን እድሜ እየበሉ ያሉትን ዝርዝሮች ማየትና ያንን ለይቶ ዝም ማሰኘት ነው።

2.ስልክዎን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች

ስልክዎትን እናጸዳለን የሚሉ መተግበሪያዎች በአመዛኙ ውሸት ናቸው። እንዲያውም ለቫይረስ ያጋልጣሉ። “ክሊን ማስትር” የሚባለው መተግበሪያ ዋንኛው ነው።

ስፔናዊው የቴክኖሎጂ አዋቂ ጆስ ጋርሺያ እንደሚለው “ክሊን ማስተር” የተባለው መተግበሪያ የስልክን ፍጥነት ይቀንሳል፣ የራሱን ገበያ ለማድመቅም ብዙ መተግበሪያዎችን እንድንጭን ያባብለናል።

የሞባይል ስልክን ፀሐይ ላይ አለመተውImage copyrightGETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫየሞባይል ስልክን ፀሐይ ላይ አለመተው

ስልክዎ ትኩሳት ከተሰማው ችግር አለ ማለት ነው። የስልክ ትኩሳት በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ለረዥም ሰዓት ለፀሐይ ብርሃን ከተጋለጠ፤ በቫይረስ ከተጠቃ፤ ወይም ደግሞ ጤናማ ያልሆነ ባትሪ ከተገጠመለት አልያም ደግሞ ያለ ዕረፍት ለብዙ ሰዓታት አገልግሎት ላይ ከዋለ ስልክ እንደ ብረት ምጣድ ይግላል።

ይህን ችግር እንቀርፋለን የሚሉ የስልክ መተግበሪያዎች ሐሰት ናቸው። መፍትሄም አያመጡም። እንዲያውም ትኩሳቱን ያብሱበታል። ስልክዎ በአዲስ መንፈስ እንዲሰራ ከፈለጉ አጥፍተው ያሳርፉት።

ለስልክዎ ጠቅላላ ጤና የሚከተሉትን ያስታውሱ

• መተግበሪያዎችን ስልክዎ ላይ ሲጭኑ ምንነታቸው ከተረጋገጠላቸው ሁነኛ የስልክ መደብሮች ብቻ ያውርዱ። አፕል ስቶር እና ጉግል ስቶር የታወቁት ናቸው።

• የፋይል ስማቸው በኤፒኬ ፊደል እንደሚጨርስ (.apk) ከሚታዩ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ

• ራሳቸውን ተአምራዊ ሥራ እንሠራለን እያሉ ከሚያሞካሹ መተግበሪያዎች ይጠንቀቁ

• ስልክዎትን በየጊዜው “አፕዴት” በማድረግ ያድሱ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here