(ኤፍ.ቢ.ሲ) ከሞባይል ስልኮች የሚወጣው ጨረር በጤንነታችን ላይ ጉዳት እንዳያስከትል በሚል ሞባይል ስልካችንን ከአካባቢያችን ራቅ እንድናደርግ በርካታ ጊዜ ይመከራል።

የአሜሪካ ካሊፎርኒያ የጤና ቢሮ ከሰሞኑ ያወጣው ማስጠንቀቂያ አዘል የጥናት ውጤት ደግሞ የሞባይል ስልክን አጠገባችን አድርገን መተኛት ለካንሰር፣ ለአእምሮ ጤና መዛባት እንዲሁም ለመካንነት ቸግር እንድጋለጥ ያመለክታል።

ጥናቱ ሞባይል ስልክን መጠቀም ምን ያክል ጉዳት እንደሚያስከትል መለየት ባይችልም፤ አጠገባችን አደርጎ መተኛት የሚያስከትለውን ጉዳት ግን መለየት እንደቻለ ተገልጿል።

የሞባይል ስልክ አጠገባችን አድርጎ መተኛት በጤናችን ላይ ገዳት የሚያደርሰው መረጃን ለማስተላለፍ በሚጠቀመው የራዲዮ ሞገድ (radiofrequency) አማካኝነት መሆኑም ታውቋል።

ለዚህ ሞደግ በተደጋጋሚ እና በጣም ቅርብ ሆኖ መጋለጥ ደግሞ ጤናችንን አደጋ ላይ ለመጣል በቂ ምክንያት መሆኑን ነው ተመራማሪዎች ያስታወቁት።

እንደ አፕል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች በምርቶቻቸው ላይ የራዲዮ ሞገድ ተጋላጭነት ማስጠንቀቂያን ለማስቀመጥ መስማማታቸውም ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች ለሞባይል ስልኮች የራዲሮ ሞገድ ያለን ተጋላጭነት በአእምሯችን እና በጆሯችን ውስጥ የካንሰር እጢ እንዲወጣ እንደሚያደርግ ማመላከቱ ይታወሳል።

የስና ልቦና ባለሙያዎች ደግሞ ለሞባይል ስለክ ያለን ቅርበት የእንቅልፍ ስርዓታችንን በማዛባት የአእምሮ ጤና ላይ ችግር ያስከትላል ይላሉ።

በሌላ ጥናትም ለሞባይል ስልኮች የራዲዮ ሞገድ ተጋላጭነት በተለይም በወንዶች ላይ የመውለድ ችግር ሊያስከተል አንደሚችል እና ይህ የሚሆነው ደግሞ የወንድ የዘር ፈሳሽ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲቀንስ በማድረግ ነው ተብሏል።

ስለዚህ ይላል ጥናቱ፤ ስማርት ስልኮችን አጠገባችን አድርጎ የመተኛት ባህል ካለን ከአጠገባችን ብናርቅ መልካም ነው ብሏል።

እንዲሁም ወደ ጆሯችን አስጠግተን ከማውራት ይልቅ የጆሮ ማዳመጫዎቸን (ሄድሴት) መጠቀምን እና በኪሳችን ከመያዝ ይልቅ ከቻልን በቦርሳ መጠቀምን መክሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here