የደቡብ ሱዳን አማፂያን መሪ ሪክ ማቻር ዛሬ ወደ ጁባ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ባለፈው መስከረም በአዲስ አበባ የተፈረመውን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ለማብሰር በተዘጋጀው ስነስርዓት ላይ ለመሳተፍ ነው ሪክ መቻር ዛሬ ጁባ የገቡት፡፡

ማቻር እ.ኤ.አ የ2016ቱ የሰላም ስምምነት ሳይሳካ ከቀረ በኋላ ወደ ጁባ ሲመለሱ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

በወቅቱ በእርሳቸውና በፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ደጋፊዎች መካከል ጦርነት ሲፈነዳ የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸሽተው ወደ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ገቡ፡፡

ከዚያም እ.ኤ.አ እስከ 2018 መጀመሪያ በቁም እስር ላይ ወደቆዩባት ደቡብ አፍሪካ አቀኑ፡፡

ባለፈው ወር ደግሞ ማቻርና ሳልቫኪር 5 ዓመታት ያስቆጠረውን ጦርነት ለመቋጨት አዲስ የሰላም ስምምነት ፈርመዋል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here