ትዕግስቴ አልቋል!

ሰሜን ኮሪያ የትኛውንም የአሜሪካ ክፍል መምታት የሚችል ነው የተባለ የረጅም ርቀት አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች።

የሰሜን ኮሪያ የቴሌቪዥን ጣቢያ፥ ፒዮንግያንግ የኒኩሌር ባለቤት ሀገር የመሆን እቅዷን አሳክታለች ሲል ዘግቧል።

North Korea claims to have successfully tested a new type of intercontinental ballistic missile, topped with a “super-large heavy warhead,” which is capable of striking the US mainland.

The country’s state media made the announcement Wednesday, hours after leader Kim Jong Un ordered the 3 a.m. launch of the Hwasong-15 missile, which reached the highest altitude ever recorded by a North Korean missile.

ሰሜን ኮሪያ ሌሊት ላይ ያደረገችው ሙከራ ሀዋሶንግ 15 ሚሳኤል የሚባል ሲሆን፥ በጣም ሀይለኛ ከተባሉት የባላስቲክ ሜሳኤሎች ውስጥ ይመደባል።

ሚሳኤሉ በጃፓን የውሃ አካል ውስጥ የወደቀ ሲሆን፥ ሰሜን ኮሪያ እስካሁን ከሞከረቻቸው ሚሳኤሎች በላይ መወንጨፉም ተነግሯል።

ኬ.ሲ.ኤን.ኤ የተባለው የሀገሪቱ የዜና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው፥ ሚሳኤሉ 4 ሺህ 475 ኪሎ ሜትር ወደ ላይ የተወነጨፈ ሲሆን፥ በ53 ደቂቃ ውስጥም 950 ኪሎ ሜትር መጓዝ ችሏል።

ሚሳኤሉ እንደ ከዚህ በፊቶቹ በጃፓን ላይ አለመብረሩና ከጃፓን የባህር ዳርቻ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወቅደቁንም ጃፓን አረጋግጣለች።

ኬ.ሲ.ኤን.ኤ አክሎም፥ ሙከራውን በይፋ ያስጀመሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገሪቱ የኒኩሌር ሀይል ባለቤት የመሆን ስራዋን ማጠናቀቋን እንዳረጋገጡ አስታውቋል።

በአሜሪካ መቀመጫቸውን ያደረጉ የተመራማሪዎች ቡድን ሰሜን ኮሪያ አሁን የሞከረችው የሚሳኤል ሙከራ እስከ 13 ሺህ ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል እና የትኛውንም የአሜሪካ ክፍል መምታት የሚችል መሆኑን እየተናገሩ ነው።

ሆኖም ግን ሚሳኤሉ ከባድ መጠን ያለው የኒኩሌር አረር በመሸከም ይህንን ሁሉ ርቀት ላይወነጨፍ ይችላል ብለዋል።

ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ አዲሱ ሀዋሶንግ 15 ሚሳኤል ከፍተኛ መጠን ያለውን የኒኩሌር አረር በመሸከም የትኛውነም የአሜሪካ ክፍል መምታት ይችላል ብላለች።

North Korea had fired 22 missiles without active warheads during 15 tests since February. US officials say North Korea is continuing to develop its missiles, rocket fuel and engines, as well as targeting and guidance systems

The US and South Korea believe Pyongyang may be able to put a miniaturized warhead on a missile sometime in 2018 — giving it the theoretical capability to launch a missile with a warhead atop it that could reach the US.

የሰሜን ኮሪያን መግለጫ ተከትሎ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ጄምስ ማቲስ በሰጡት አስተያየት፥ “እውነቱን ለመናገር የአሁኑ የሚሳኤል ሙከራ ከዚህ በፊት ከተደረጉ ሙከራዎች ከፍተኛው ነው” ብለዋል።

የሰሜን ኮሪያ ተግባርም ዓለምን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንት ዶላልድ ትራምፕም ሚሳኤሉ አየር ላይ እያለ ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፥ ጉዳዩን በትኩረት እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።

የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራውን ተከትሎም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

ፒዮንግያንግ ለመጨረሻ ጊዜ የሚሳኤል ሙከራ ያደረገችው በመስከረም ወር ሲሆን፥ በወቅቱም ስድስተኛውን የኒኩሌር ሙከራ አድርጋ ነበር።

የተለያዩ የዓለም ሀገራት የሀገሪቱን ተግባር በመኮነን የተለያዩ ማእቀቦችን ቢጥሉባትም ሰሜን ኮሪያ ግን የሚሳኤል እና የኒኩሌር ማበልፀግ መርሃ ግብሯን አጠናክራ ቀጥላለች።

አሜሪካ የዓለም ሀገራት ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላቸውን የዲፕሎማሲ እና የንግድ ግንኙነቶችን እንዲያቋርጡ ጠየቀች።

ዋሽንግተን ይህን ያለችው ፒዮንግያንግ ትናንት የረጅም ርቀት አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ ነው።

በመንግስታቱ ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ኒኪ ሃሌ በፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት፥ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና ለፒዮንግያንግ የምታደርገውን የነዳጅ አቅርቦት እንድታቋርጥ ጠይቀዋል።

አሜሪካ ግጭት እንዲፈጠር እንደማትፈልግ የተናገሩት አምባሳደሯ፥ ጦርነት ከተነሳ ግን የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ እንደሚደመሰስ ገልፀዋል።

ኒኪ ሃሌ ይህን ማስጠንቀቂያ የተናገሩት ሰሜን ኮሪያ ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ የመጀመሪያዋን የሚሳይል ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ ነው።

ሰሜን ኮሪያ በበኩልዋ ትናንት ሌሊት ላይ ያደረገችው የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራ በ4 ሺህ 475 ኪሎ ሜትር ከፍታ መምዘግዘግ የሚችል ሲሆ፥ ይህም ዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ማዕከል ከሚገኝበት ከፍታ 10 እጥፍ እንደሚርቅ አስታውቃለች።

የሞከረችው የባሊስቲክ ሚሳኤል ከእስካሁኖቹ የላቀ መሆኑን የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here