የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ አቶ መላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ

የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ በሙስና ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ።

ከሁለቱ ግለሰቦች በተጨማሪም አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ፣ አቶ ከተማ ከበደ፣ አቶ ጌቱ ገለቴ፣ አቶ ገብረስላሴ ገብሬ፣ አቶ ስማቸው ከበደ፣ ኮሎኔል ሀይማኖት ተስፋው፣ አቶ ገምሹ በየነ፣ ጂ ኤች ሲ ኔክስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ጌታስ ኩባንያ፣ ኮሜት፣ ነፃ ትሬዲንግ እና ፍፁም ገብረመድህን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ይገኙበታል።

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ በሙስና ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ዓለማየሁ ጉጆ፣ አቶ ዋስይሁን አባተ፣ አቶ አክሎክ ደምሴ፣ አቶ ዛይድ ወልደገብርኤል፣ አቶ መስፍን ወርቅነህ፣ ወይዘሮ ሰኸን ጎበና፣ አቶ ጌታቸው ነገሪ፣ አቶ ነጋ መንግስቱ እና አቶ ሙሳ መሀመድ የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ አቃቤ ህግ ክሳቸውን እንዳቋረጠና ዛሬውኑ ከማረሚያ ቤት እንደሚወጡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

በተጨማሪ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ የተለያዩ ግለሰቦች የግንቦት 20 የድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ክሳቸው ተቋርጧል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here