ከባለስልጣኑ ባገኘነው መረጃ መሰረት አሁን ላይ አውሮፕላኖች መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡

በረራዎችም ሰዓታቸውን ጠብቀው አውሮፕላን ማረፊው ወደ መደበኛ ስራው ተመልሷል፡፡

የሃገር ውስጥ በረራዎችም ያለምንም ችግርና መስተጓጎል አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የበረራ ተቆጣጣሪዎች ችግር ምክንያት የቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የበረራ አገልግሎት መስተጓገሉ ተገለጸ፡፡

የኤርፖርቶች ኦፕሬሽን ማናጀር አቶ ንጉሴ ሙሉጌታ በሰጡት መግለጫ የበረራ ሰራተኞቹ ተቃውሟቸውን ማሰማት የጀመሩት ከትላንትናው እለት ጀምሮ ነው ብለዋል፡፡

እናም በአሁኑ ሰዓት የአየር መንገዱ አለም አቀፍ በረራዎች ሙሉ በሙሉ መቆማቸውን ነው የተናገሩት፡፡

የሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው አለም አቀፍ በረራዎቹ ሙሉ በሙሉ የተቋረጡ ሳይሆን አሁን በተፈጠረው ችግር የበረራ መስተጓጉል ነው ያጋጠመው ብለዋል፡፡

ይህንንም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚስተካከል ነው የተናገሩት፡፡

የበረራ ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ የሚያቀርቡት ጥያቄ ከበዓል ቀናት አበል ክፍያ እና ሌሎች ጉዳዮች መሆኑን ነው ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው የገለጹት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here