# ዛሬ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚደንት ወይም እርስ ብሄር ተሹሟል።

ሴቶችን ወደ ስልጣን ማምጣት የሚበረታታ እና ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው!!!

ነገር ግን የዛሬው ሹመት የሐገሪቱ እርሰ ብሄር ካለው ስልጣን አንፃር እና ከተሾሙት እንስት የስራ ልምድ እና የትምህርት ዝግጁነት አንፃር የሰው ሐብት ማባከን ነው!!

ከብሔር ውክልና አንፃር ታይቶም ከሆነ አግባብነት የሌለው ፣ የይስሙላ ውክልና ነው!

# በፖርላሜንተሪ የመንግስት አወቃቀር እርእሰ ብሄር እና እርእሰ መንግስት ይኖራል።

በአብዛኛው የመንግስት ትልቁን ስልጣን የሚይዘው እርእሰ መንግስት( ሄደው ኦፍ ገቨርንመት) ነው።

# የእርእሰ ብሔርን ስልጣን አስመልክቶ ሁለት አይነት አሰራር አለ።

አንደኛው እስታንደርድ ሞዴል ሲሆን እርእሰ ብሄር( ሄድ ኦፍ ዘ እስቴት) የአስፈፃሚነት ስልጣን ይኖረዋል።

ነገር ግን በሄድ ኦፍ መንግስት አማካሪነት ይሰራል። የህንድ፣ ዩናይትድ ኪንግደም ምሳሌ መውሰድ ይቻላል።

ሁለተኛው መንገድ የተወሰነ የአስፈፃሚነት ስልጣን ለእርእሰ ሀገሩ የሚሰጥበት መንገድ ነው።

# እንግዲህ በሁለቱም መንገድ ለእርሰ ሐገር( ሄድ ኦፍ ዘ እስቴት) የአስፈፃሚነት ስልጣን ይኖረዋል።

ዋናው ምክንያትም እርእሰ ብሄር ወይም እርእሰ ሐገር የአንድ ሐገርን ህዝብ ስለሚወክል፣ የሐገር ምልክት ስለሆነ፣ ህዝቦችን አንድ የማድረግ ሀላፊነት ስላለበት፣ የዜጎች መሪ ስለሆነ ፣ መንግስት እና ሐገር ችግር ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ የእሱ አመራር አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

በሌላ መልኩ እርእሰ መንግስት ከአሸናፊ ፖርቲ ስለሚሾም ውክልናው ሙሉ አይደለም።

በአንዳንድ ሐገራት እርእሰ ሐገር የመከላከያ የበላይ አዛዥ ፣ የህገ መንግስት የበላይ፣ አንዳንድ የገለልተኛ ተቋማት ሹመት( ዳኞች፣ የብሄራዊ ባንክ ገዢ) ፣ የመንግስት መሪው ምክትል፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ፣ የመሳሰሉት ስልጣኖች ይኖሩታል። ህንድ፣ እስራኤል፣ ሩሲያ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል።

# በእኛ ሐገር እርእሰ ብሄር ያለው ስልጣን እዚህ ግባ የማይባል ነው። እንግዳ መቀበል፣ አምባሰዳር መሾም እና መቀበል፣ ማእረግ መስጠት የመሳሰሉ ተፅኖ መፍጠር የማይችሉ ስልጣኖች ነው ያለው።

# በሌላ መልኩ ሐገሪቱ የምትመራው በአራት ፖርቲዎች ጥምረት ነው። ውክልናው ሙሉ አይደለም። በተቃራኒው የአስፈፃሚው ጠቅላላ ስልጣን በእርእሰ መንግስቱ ስር ነው።

# ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት በሐገሪቱ በነበረው ችግር የአመራር ክፍተት እንደ ተፈጠረ ግልፅ ነው። አራቱ ፖርቲዎች በፖለቲካ መሳሳብ ችግር በሚገጥማቸው ጊዜ ሀገሪቱም ችግር ውስጥ ትወድቃለች ።

የመንግስት መሪ መምራት በማይችልበት ጊዜ( አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ እንዳልመራ ተደርጌ ነበር ያሉትን፣ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስተርም ልታሰር ነበር፣ የግድያ ሙከራ መደረግ) ፣ መሪ ቦታ እስከሚይዝ ድረስ ክፍተት የሚሞላ ገለልተኛ፣ ስልጣን ያለው ፣ የሐገር እና የህዝብ ተወካይ ያስፈልጋል።

ለምሳሌ ኢህአዴግ ዲሞክራቲክ ሴንትራሊዝም ባይከተል( የበላይ አመራር ውሳኔን መቀበል) እና ሐገር ችግር ውስጥ ብትገባ ባለፉት ጊዜያት እንደታየው፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ እንዴት ሐገር ማረጋጋት ይቻል ነበር??

አራቱ ፖርቲዎች አለመስማማት ደረጃ ላይ ቢደርሱ ለጊዜው ክፍተት እንዴት ሊሸፈን ይችላል?

መሪው መንግስት ከፖለቲካ ጥቅም አንፃር ወይም ባለመስማማት ከክልሎች አቅም በላይ የሆነን የፀጥታ ችግር ለመፍታት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ባይችል ምን አማራጭ ይኖራል?

# ባለፈው አንድ ቃለ መጠይቅ ላይ ዶ / ር ሙላቱ ተሾመ ተሰናባቹ እርእሰ ብሄር ፣ የእርእሰ ብሔሩ ስልጣን መስተካከል አለበት ብለው ነበር።

# ሴት እርእሰ ብሄር ከመሾም ባለፈ ህግ መንግስቱን በማሻሻል የእርሰ ብሄሩን ስልጣን ማሻሻል አስፈላጊ ከመሆኑም በላይ ፣ አስፈላጊነቱ በተሞክሮ ጭምር የታየ ጉዳይ በመሆኑ ፣ መታሰብ ያለበት ጉዳይ ይመስለኛል!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here