ከተነሣ አይቀር፣ ምናልባት ልብ የሚል አይጠፋም ከሚል፣ ስለ አዲሷ ፕሬዚዳንት የሚከተለውን እናስታውስ።

1፤ ቃለ ማሃላ፣ እኔ እገሌ

መቼም የእኛና የማዕረግ ነገር ጉድ ነው። ዛሬ ጠዋት ፕሬዚዳንቷ ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት መሃላውን አስፈጻሚ ነበሩ። እንደማንኛውም ማሃላ “እኔ እገሌ” ብሎ መጀመር ያለ ነው።

መሃላ አስፈጻሚው “እኔ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ” አሉ።

ተሿሚዋ ግ ን “እኔ ሳህለወርቅ ዘውዴ” ብለው ደገሙ።

ተሿሚዋ በሥራ ልምዳቸው የሚያውቁት፣ በትህትናም የተዉት ቁልፉ ነገር በቃለ ማሃላ ወቅት የራስን ማዕረግ መጥራት አስፈላጊም የተከበረ ባህልም እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነው።

ለወደፊቱ፣ በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በቀር፣ በቃለ ማሃላ ወቅት ማዕረግ መጥራት አይገባም።

የፓርላማው ፕሮቶኮል፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቢሮ ሁሉ እንዲያውቁት ይሁን።

እርግጥ ማዕረግ እየደረቱ መኮፈስ ልማድ በሆነበት፣ እየፈጠሩ ጭምር ማዕረግ መደረት አዋቂነት በሚመስላቸው ጋዜጠኞች አቀጣጣይነት በደነደነው ባህል መሠረት ከሔድን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኛ አልተሳሳቱም።

ጋዜጠኞቹም ቢሆኑ ወዲያውኑ “ፕሬዘዳንት አምባሳደር ሳህለ ወርቅ” እያሉ መጻፍ ጀመሩ። መቼም መጠየቅና ማፈር የለም።

ይኼ ወደ ሁለተኛው ነጥብ ይወስደኛል።

2፤ ስም አጠራራቸው

የፕሬዚዳንቷ ጽ/ቤት ክብርትነታቸው እንዴት መጠራት እንዳለባቸው እና እንደሚፈልጉ አጥንቶ ሥራውን መምራት፣ እገረ መነገዱንም ደናቁርትን ማስተማር እንዳለበት ማስታወስ ይኖርብናል።

ማዕረግ መደረት ለመኮፈስ ካልሆነ ክብር አይጨምርም።

በተወሰኑ ሁኔታዎች ካልሆነ በቀር ማዕረጎች መጠራት ያለባቸው ተገቢ በሆኑበት አውድ ብቻ መሆን አለበት።

ለዚያውም መጠሪያ የሚሆኑ እና የማይሆኑ ማዕረጎች እንዳሉና ተለይተው መታየት እንዳለባቸው ሳንዘነጋ ነው።

የአንድ አገር ርዕሰ ብሔርነት ከሁሉም የሚበልጥ ክብር ያለው ማዕረግ ነው።

ተሿሚው በቢሯቸው እስካሉ እና በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በቀር ከዚህ ማዕረግ እኩል ሊጠሩበት የሚገባ ሌላ ማዕረግ ሊኖር አይገባም።

አምባሳደርነት ከፕሬዚደንትነት እኩል የሚጠራ አይደለም። በአንጻራዊነት ሲታይ በጣም ዝቅተኛ ማዕረግ ነው። ስለዚህም ርዕሰ ብሔር (ፕሬዘዳነት) ሳህለወርቅ ናቸው።

(ርዕስ በሴት ጾታ የተለየ አገባብ ካለው አረጋግጬ አርማለሁ።)

Sahle-Work Zewde becomes Ethiopia's first female president

Sahle-Work Zewde becomes Ethiopia's first female president

Posted by DAILY NATION on Thursday, October 25, 2018

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here