ኢንጅነር ህይወታቸው አልፎበት የተገኘው መኪና ፖሊሶች በቦታ እስከሚደርሱ ሰአት ድረስ 
የመኪናው ሞተር አልጠፋም፡፡

መኪናው የቆመበት መኪና ሀገር አቋራጭ መኪኖች የሚቆሙበት ቦታ ነው ስለዚህ ከዋናው መንገድ ወጥቶ ነው የቆመው፡፡

በተጨማሪው መኪናው በትክክል ነው park የተደረገው፡፡

የመኪናው በሮችና መስኮቶች በሙሉ ዝግ ነበሩ፡፡

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የተለቀቁት ፎቶዎች ላይ ኢንጂነር የነበሩበት መኪና በሁዋላ በኩል ያለች የመኪናው መስኮት እንደተሰበረች አይተናል::

ሆኖም መስታወቷ የተሰበረችው በፖሊሶች ነው የመኪናዎቹ በሮች ስለተቆለፉ ለመክፈት ሲባል ነው የተሰበረችው፡፡

ፖሊሶች በቦታው ዘግይተው ነው የደረሱት ከዛም በተጨማሪ ባለ ስልጣናትም በቦታው ተገኝተዋል፡፡

የፎረንሲክ ቡድኖች እንዲሁም መርማሪ ፖሊሶች መረጃዎችን ሰብስበዋል፡፡

አስከሬናቸውም በአምቡላንስ ተጭኖ በፖሊሶች አጃቢነት ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሄስፒታል ለምርመራ ተወስዷል፡፡

የኢንጂነር አስከሬን ከተወሰደ በሁዋላ መኪናዋን ሲቪል የሆነ ሰው #ብቻውን አስነስቶ የትራፊክ መብራት እየጣሰ ወደ ቤተመንግስት አቅጣጫ እንደነዳት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

እስካሁን ድረስ በጥይት ተመተው ከመሞታቸው ውጭ ፖሊስ ያወጣው መረጃ የለም፡፡

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን አሟሟት የሚገልፁ መረጃዎችን ፖሊስ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

እንዴት እንደ ሞተ – መረጃዎች እና ማስረጃዎችን ይዘናል፤

በቅርቡ ቀን ይፋ እናደርጋለን –  ኮምሽነር ጄነራል ዘይኑ ጀማል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here