ሶማሊያየጸጥታው ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ አለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ የሚያስችል አቅም ፈጥሬያለሁ ብላለች፡፡

የሶማሊያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አብዲቃኒ ሳዒድ አረብ በአዲሱ የፈረንጆች አመት የውድድር መርሀ ግብሮችን በሜዳችን ማድረግ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

“በሀገሪቱ ያለው ፀጥታ ድሮከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ ሰላም እና መረጋጋት ተመልሷል ብለዋል፡፡

የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት የሶማሊያ ዜጎች ብሄራዊ ቡድናቸው በሜዳው ሲጫወት የመመልከት መብት እንዳላቸው ጠቅሰው በ2018 በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ብሄራዊ ቡድኖችን ለወዳጅነት ጨዋታ ወደ ሞቃድሾ እንደሚጋብዙ ተናግረዋል፡፡

ፅንፈኛው የሽብር ቡድን አልሻባብ በሶማሊያ መሽጎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ግድሏል በሚሊዮን የሚቆጠሩት እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል፡፡

በዚህም የተነሳ ሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት በመጣቷ እኤአ 1998 በኋላ አለም አቀፍ ውድድሮችን በሜዳዋ አስተናግዳ አታውቅም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here