ሽረ እንዳስላሴ ጅማ በአባ ቡናን በማሸነፍ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለ ሶስተኛው ቡድን መሆኑን አረጋገጠ።

በዛሬው ዕለት በሀዋሳ በተካሄደው ጨዋታ ሽረ እንዳስላሴ ጅማ አባ ቡናን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለው።

በ2005 ዓመተ ምህረት የተመሰረተው ሽረ እንዳስላሴ በአጭር ጊዜ ውስጥ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ አድጓል።

በሌላ በኩል ቀድመው ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀሉት ባህርዳር ከነማ ና ደቡብ ፖሊስ ያደረጉት ጨዋታ በደቡብ ፓሊስ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ደቡብ ፓሊስ ባህርዳር ከተማን አደማ ላይ የተካሄደውን ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው የከፍተኛ ሊጉ ቻምፒዮን መሆን የቻለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here