በሕማማት ሳምንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለየት ያለ የአገልግሎት ሥርዓት ሠርታለች፡፡

ከጸሎተ ሐሙስ በቀር ቅዳሴ አይቀደስም፡፡ይህ ብቻም አይደለም፡፡

የዘወትር የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሆነው ሥርዓተ ጥምቀተ ክርስትና ፣ሥርዓተ ፍትሐት፣ሥርዓተ ማኀሌት፣ሥርዓተ ተክሊልና ሌሎችም የተለመዱ አገልግሎቶች አይካሄዱም፡፡

በመስቀል መባረክ ፣ኑዛዜ መስጠትና መቀበል እግዚአብሔር ይፍታህ ማለት የለም፡፡

በአጠቃለይ ከዓመት እስከ ዓመት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ለምእመናን ይሰጡ የነበሩ መንፈሳውያት አገልግሎቶች አቁመው

በሌላ ወቅታዊ ማለትም

የጌታችንን ሕማሙን ፣መከራውን፣መከሰሱን፣በጲላጦስ ዐደባባይ መቆሙን፣መስቀል ላይ መዋሉን ሐሞት መጠጣቱን እና ሌሎችንም ለኃጢአተኛው የሰው ልጅ ሲባል የተከፈለውን ዕዳ የሚያስታውሱ አግልግሎቶች ይተካሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here