(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በግል ባለሃበቶች እና በመንግስት ተቋማት ተይዘው ያለልማት የተቀመጡ 67 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት እስከ ስድስት ወር እንዲያለሙ አስገዳጅ ውል እየገቡ ነው።

የመዲናው አስተዳደር የመሬት ባንክ እና ማስተላለፍ ፅህፈት ቤት የዴስክ ክትትል ዳይሬክተር አቶ በየነ ላጲሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የግል ባለሃብቶቹ እና የመንግስት ተቋማቱ በገቡት አስገዳጅ ውል መሰረት ካላለሙ የወሰዱት መሬት እንዲነጠቁ ይደረጋል።

የተሰጠው የመጨረሻ የአስገዳጅ ውል መፈረም ከሚገባቸው 68 የግል ባለሃብቶች እና የመንግስት ተቋማት 31 ብቻ ናቸው አስገዳጅ ውሉን የፈረሙት።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ እየቀረቡ እንደሚፈርሙ ይጠበቃል ሲሉ ዳሬክተሩ ገልፀዋል።

የግል ባለሃብቶቹ እና ተቋማቱ በስደስት ወራት ውስጥ ወደ ልማት ካልገቡ ገን መሬቱ መንግስት እንደሚነጠቅ ተገልጿል።

በታሪክ አዱኛ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here