አስቸኳይ ማሳሰቢያ !!!

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ኅዳር 26 ቀን 2011 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ “ብሄር እና የብሄር ድርጅት መጥፋት አለባቸው፡፡” ፣ “ሕገመንግስቱ ክብር የለውም።” እና “እኔ እዚህ የመጣሁት ዶክተር አብይን ለማገዝ ነው፡፡” አሉ ተብሎ በሶሻል ሚድያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት መሆኑን አሳውቃለሁ፡፡

ሆኖም ግን በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ የተናገርኩትን አጠር አድርጎ፤ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የነበሩት አቶ ሰለሞን በላይ እንደዚህ አቅርቧቸዋል፡፡

1) የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብር ከተፈለገ ጫፍ አልባ ውይይት (endless conversation) ያስፈልጋል ይላል፡፡ በንግግር ተዋስኦ የሚመጣው ችግር በበለጠ ንግግር ማሸነፍ ይገባል እንጅ በስሜት እና ሃይል መሆን የለበትም ፤ከነጻ ንግግር የሚመጣን ችግር ለመፍታት የበለጠ ነጻ ንግግር (more free speech) መፍቀድ እንደሚገባ፣

2) ወቅታዊ የፓለቲካ ሁኔታን በተመለከተ አልፋ እና ኦሜጋ በሚል ርዕስ ስለ አማራ እና ኦሮሞ ግንኙነት ያመጣውን ለውጥ በማድነቅ በመከባበር/በመገናዘብ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መቀጠል እንዳለበት ይህን ግንኙነት ሌሎችም ህብረተሰብ ለአዎንታዊ ሚና ሊጠቀሙበት እንደሚገባ፣

3) ወጣቱ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ሀሳብ እንድያራምድ እና እንድመረምር ብሎም ለዴሞክራታይዜሽን ፣በህግ የበላይነት እና በተጀመረው ለውጥ ላይ ያለውን ሚና፣

4) ወጣቱ ጠያቂ እና ተሟጋች መሆን አለበት። ሀሳቡንም በነጻነት እንድያቀርብ በማለት የሶክራቲስን “የማንመረምረው ህይዎት እርባና የለውም ” እንድሁም ኢትዮጲያጲያዊዉ ፈላስፋ ንጉስዘርያቆብ “መርምሮ ተመራምሮ የተሻለውን መንገድ እንያዝ ” እንዳለው ሁሉ በእያንዳንዱ ድርጊት እና ውሳኔያችሁ ላይ “ልንሳሳት እንችላለን ብላችሁም” በአስተውሎት እና በጥንቃቄ መሆን እንዳለበት፣

5) ኢትጵያዊው ፈላስፋ እጓለ ገብረ ዮሐንስ “የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ” በተሰኘ መጽሐፋቸው መግቢያ ላይ አውሮጳ፣ በጀርመን ሀገር ሳሉ ላዩት ለዚያ ዘመን ወጣት መንፈስ መጽሐፋቸውን እንደመታሰቢያ ሲያቀርቡ “በከፍተኛ መንፈስ ለተነሳው ወጣት እጅ መንሻ እንድሆነኝ ማለታቸው በወቅቱ ስለነበረው ለመማር፣ ለማወቅ፣ አገርን ለመለወጥ የሚያስብ መንፈስ እንደነበረ የአሁኑ ወጣትም በዚህ መንፈስ መሰረት ለማወቅ ለራሱ እና ለሀገሩ ዕድገት መስራት እንዳለበት፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here