አብዛኛው መራጭ በተፈለገው ያክል ድምጽ እንዳይሰጥ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ የድምጽ መስጫ ቦታው መራቅ እና ወደ ስፍራው ያለመሄድ ፍላጎት እና አቅም ማጣት ነው፡፡

የ”Election Attitude” ጸሃፊ የሆኑት ጆን ፓትሪክ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚከናወኑ ምርጫዎች ወደ ጠንካራ የምርጫ ስርዓት ዙሪያ እንደሚወስዱ ሃሳቦቹን ሰንዝሯል፡፡

የቀድሞው የምርጫ ድምጽ አሰጣት ስርዓት በአብዛኛው ስራ የሚበዛባቸውን፣ አቅመ ደካሞችን፣ ታማሚዎችን ያማከለ አይደለም ሲሉ ሃሳብ የሰነዘራል፡፡

በተጨማሪ ሌሎች በመቶ የሚቆጠሩ ምክንያቶች መራጮች ድምጽ ወደ ሚሰጥበት ቦታ እንዳይሄዱ እና ድምጻቸውን እንዳይሰጡ እንቅፋት እንደሚሆኑ ይነገራል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች መራጮች ተፈላጊውን ድምጽ ባሉበት ስፍራ ሆነው በስማርት ስልኮቻቸውን በመጠቀም ድምጽ እንዲሰጡ የሚያስችል የብሎክቼይን #blockchain ቴክኖሎጂን በመሞከር ላይ ይገኛሉ፡፡

የብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂም በታሪክ ውስጥ ከተከሰቱ እጅግ ደህንነቱ የተጠበቀ የዴታ መላላኪያ አማራጭ ሲሆን ማንኛውም አካል በፈለገው መገልገያ መሳሪያ ላይ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ሲስተም ነው፡፡

የብሎክ ቼይን ከድጂታል ገንዘብ ዝውውር ጋር ከፍተኛ ትስስሮች ያሉት ሲሆን ቢትኮይንን በመሳሰሉ የዲጂታል ገንዘቦች ጋርም ከፍተኛ ቁርኝት አለው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን በሚይዙ በጤና ተቋማት እና በምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ላይም መተግበር ጀምሯል፡፡

ብሎክ ቼይን እና ደህንነቱ ተጠበቀ የድምጽ አሰጣጥ

ብሎክ ቼይን ቴክኖሎጂ ያልተማከ የኮምፒውተር ኔትዎርክ ስርዓትን ስላለው ሁሉም ተጠቃሚ የራሱ የሆነ ተግባራትን የሚከውን ሲሆን ሁሉም መረጃ በአንድ ስፍራ ላይ እንዳይከማች የሚያደርግ ሲሆን መረጃዎች ላልተፈለገ አላማ እንዳይውሉ እና ዴታዎች የሚያደርግ ስርዓት ነው፡፡

አይበለው እና የስማርት ስልክ እና ላፕቶፖች በመረጃ ጠላፊዎች አልያም አቨጭበርባሪዎ እጅ ቢወድቅ፣በቫይረስ እና በአጥፊ ሶፍትዌሮች ጥቃት ቢደርስባቸው እንኳ የብሎክ ቼይን የድምጽ ሲስተሙ ደህንነቱ የተጠበቀ እንደሚሆን በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፈሰር የሆኑት ዳቪድ ዲል ይናገራሉ፡፡

ከ2016 ጀምሮ በብሎክቼይን ሲስተም አማካኝነት በግል ምርጫዎች ላይ በተሳተፉ 8 ሚሊዮን የሚሆኑ መራጮች በቴክኖሎጂው አማካኝነት ድምጽ መሰጠቱም ይነገራል፡፡

የቴክኖሎጂው ኩባንያዉም በ2018 በሚካሄደው የአጋማሽ ምርጫ ዘመን የአሜሪካ ምርጫ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ይህ ቴክኖሎጂም ሙሉ ለሙሉ ተቀባነት ሲያገኝ እና ተግባራዊ ሲሆን የምርጫ ማጭበርበሮችን ከማስቀረት በተጨማሪ በምርጫ የሚሳተፉ አካላትን በማበረታታት ባሉበት ሁነው ድምጽ በመስጠት ተሳታፊ የሚያደርግ ወሳኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የቴክኖሎጂ ስርዓት ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here