የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በሰኔ 16ቱ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ

የስራ ከፍተት አሳይተዋል ተብለው በተጠረጠሩት ላይ  14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተጠይቆ የመጨረሻ  የሶስት ቀን  ጊዜ ተሰጠ።

የቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን እና ዘጠኝ በተለያዩ ሃላፊነት ደረጀ ላይ የሚገኙት የፌዴራል ፖሊስ አበላት

ዛሬ ለተሰጣቸው የመጨረሻ የምርመራ የጊዜ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድቤት 1ኛ የጊዜ ቀጠሮን በሚመለከት ወንጀል ችሎት ቀጠሮን ለመከታተል ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ በነበረው የችሎት ቀጠሮ የተገኘው መርማሪ ፖሊስ በመዝገብ ቁጥር 264464 በስራ ክፍተት በሚል የተጠረጠሩትን 10 ተጠርጣሪዎችን

በተሰጠው የመጨረሻ የአራት ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከሃላፊዎች ጋር ምርመራውን መገምገሙን በመግለጽ

ምስክር ለመቀበል በክፍለ ሃገር የተላኩ አባላትን መልስ ለመጠበቅ እና የተጨማሪ ምስክርና የተላኩ ደብዳቤዎችን ለመሰብሰብ

ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ይሰጠኝ ሲል መርማሪ ፖሊስ ፍርድቤቱን ጠትይቋል።

በቀዳሚነት የቀረቡት ምክትል ኮሚሽነር ግርማ በበኩላቸው ለምርመራ በሚል ለአምስተኛ ጊዜ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቁ

ህግን የተከተለ አይደለም ያሉ ሲሆን፥ በተሰጣቸው የመጨረሻ ጊዜም የያዙት ተጨማሪ ተጠርጣሪ የለም ብለዋል።

የምክትል ኮሚሽነሩ ጠበቃም መርመሪ ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዛዝን እያከበረ አይደለም ፍርድ ቤቱ

ለመጨረሻ ጊዜ ብሎ የሰጠውን የአራት ቀን ጊዜ ምንም ሳይሰራ በድጋሚ መጠየቁ ፍርድ ቤቱን አለማክበር ነው ብለዋል።

የዋስትና መብትን በማያሳግድ የአሰራር ክፍተት ጥርጣሬ ብቻ ከአንድ ወር በላይ አስሮ ማጉላላት ህገ መንግስትን የተከተለ አለመሆኑን ገልፀዋል።

ቀሪ ዘጠኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላተም በተመሳሳይ እኛ ዘቅተኛ የኢኮኖሚ አቅም ያለን ተከራይተን መኖር አቅቶን

በካምፕ እየኖርን ህዝብና ህገ መንግስቱን ስንጠበቅ የኖርን ዜጎች በመሆናችን መብታችን ሊጠበቅ ይገባል በማለት ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ እንደማይገባና ከዚህ በፊት የፖሊስ ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ምርመራ መጠናቁን በሚዲያ አቅርበዋል ብለዋል።

በመሆኑም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ አልጨረስኩም እያለ ሊያስረን አይገባም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስን በዋስ ቢወጡ የሚያደርሱት ችግር እንዲገልፅ የጠየቀ ሲሆን፥

መርማሪ ፖሊሱም ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ ሰነዶች ሊያጠፉ ይችላሉ በማለት ዋስተናውን ተቃውሟል።

ጉዳዩን የተከታተለው ችሎት የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄ ለአምስተኛ ጊዜ በማለፍ

ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጊዜ እንዳይጠይቅ በማሳሰብ ምርመራወን ጭርሶ እንዲቀርብ ለመጨረሻ ጊዜ የሶስት ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here