በቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ጆሞ ኬንያታ የጋራ መሠረት ታቅዶ ተጥሏል፤ የእኔና አንተ – የዚህ ትውልድ ተግባር እቅዱን በሥራ መተርጎም ብቻ ነው፡፡ አዲስ የምናቅደው ነገሮች የሉንም››

ከ60 ዓመት በፊት ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ መከላከያ አፍርተናል፡፡ ኬንያ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የዲፕሎማሲያዊ የክብር ግንኙነት አለን፡፡

ኬንያ እና ኢትዮጵያ – ያለ ቪዛ እንወጣለን ፤ እንገባለን፡፡ ኢትዮጵያ ቤታችን ነው፡፡ ኬንያ ቤታችሁ ነው፡፡

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የስምንት ዓመት ልጅ እያለሁ ‹‹አዲስ›› የምትባል ውሻ አበርክተውልኝ ነበር፡፡ ሞይ፤ አባታችን ሲያርፍ አልተመቻትም መሰል እርሱን ተከትላ ሄደች፡፡

በቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ጆሞ ኬንያታ በቤተ መንግሥት እንደመከሩት ሁሉ፤ የአባቱ ልጅ የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በቤተመንግሥት በይፋ በተለያዩ ሁለትዮሽና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ሞያሌ እና ኬንያ ሞያሌ ከተሞችን እንደ ዱባይ፤ የንግድ ማዕከል ለማድረግ እንታትር ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አለምአቀፍ ሽብርተኞችን ለመዋጋት እና በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማምጣት ጥረት ላይ ተቀናጅተው ለመስራት ተፈራርመዋል ።

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት ለሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ከፍተኛ ባለስልጣናት ልዑክ ወደኬንያ አምርቶ ትላንት ተመልሷል፡፡

በነገራችን ላይ … (ከውስጥ አዋቂ ባገኘሁት መረጃ መሰረት)

የኬንያዉ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እንዲህ አሉ፤ ‹‹እኔ በኬንያ ወጣቱ መሪ እባላለሁ (ምክንያቱም አባቱ፤ ጆሞ ኬንያታ እና ኪባኪ ሽማግሌዎች ነበሩ፡፡ ኡሁሩ መንበረ ሥልጣን የተረከቡት በ 50 ዓመታቸው ነበር) … እኔ በኬንያ ወጣቱ መሪ እባላለሁ፡፡ ከኔ በላይ ወጣት መሪ ኢትዮጵያ አፍርታለች›› አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው፤ ‹‹ከታላቁ ወንድሜ፤ ከኡሁሩ ብዙ እማራለሁ›› ብለው አስፈንድቋቸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here