1. በባዶ ሆድ ውሃ መጠጣት አንጀትን በማጽዳት ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ
የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲመጥ ይረዳናል፡፡

2. አዲስ የደም እና የጡንቻ ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋል።

3. ክብደትን ለመቀነስ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍዎ ሲነሱ ቀዝቃዛ
ውሃ መጠጣት ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፡፡

4. ሲያዩት የሚያምርና ጤናማ የሆነ ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

ውሃ በደም ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ነገሮችን ጠራርጎ በማስወጣት ቆዳችን ንጹህ፣
ለስላሳና አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

5. የሊምፍ ሥርዓታችን (Lymph System) የተመጣጠነ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

እነዚህ ዕጢዎች የዕለት ከዕለት ተግባራችንን በትክክል እንድንወጣ፣
የሰውነታችን ፈሳሽ የተመጣጠነ እንዲሆን እና ኢንፌክሽንን እንድንዋጋ
ይረዱናል፡፡

ውሃን በመጠቀም የሚደረግ ህክምና

በአሁኑ ጊዜ ከወደ ጃፓን የመጣ አዲስ ልምድ አለ ጃፓኖች በሚመገቡበት ጊዜ
ትኩስ ሻይ ይጠጣሉ ይህም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው ህክምና ሲሆን ይህ
ህክምና ከጠዋት ጀምሮ ቀኑን ሙሉ በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ውሃ መጠጣትን
ያካትታል፡፡

ይህም ህክምና በሚጀምሩበት ሰሞን በተደጋጋሚ ሽንት መሽናት
የሚያጋጥም ሲሆን በጃፓን የህክምና ማህበር ከብዙ በሽታዎች የመፈወስ
አቅሙ 100% መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ከነዚህም በሽታዎች መካከል የራስ ህመም፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም፣ የልብ
ህመም፣ አርትራይተስ፣ ለፈጣን የልብ ምት፣ ለሚጥል በሽታ፣ ለአስም፣ ቲቢ፣

መንጋጋ ቆልፍ፣ ለኩላሊትና ሽንት በሽታ፣ ማስመለስ፣ ጨጓራ፣ ተቅማጥ፣ ለሆድ
ድርቀት፣ ለሁሉም የአይን በሽታ፣ ለካንሰርና የወር አበባ ችግር፣ ለጆሮ አፍንጫና
ጉሮሮ ህመሞች ፈውስ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት

ምግብ በምንመገብበት ጊዜ ቀዝቃዛ ውሃ መጠጣት የራሱ የሆነ የጐንዮሽ
ጉዳቶች አሉት፡፡

በተመገቡት ምግብ ውስጥ የሚገኝው ዘይት እንዲወፍር
ያደርገዋል፤ ይህ ማለት የምግብ ስልቀጣ ሥርዓትን ከማዘግየቱ በተጨማሪ

ምግብን ከሚፈጨው አሲድ ጋር ግጭት ይፈጥራል፤ አንጀታችን ምግብን
በፍጥነት ይመጣቸዋል፣ ወደ ስብ(ፋት) ይቀይራቸዋል

ስለዚህ ከምግብ በኋላ
ያልቀዘቀዘ ወይም ትንሽ ለብ ያለ ውሃ ወይም ሾርባ ይጠቀሙ፡፡

ህክምናው እንዴት ይተገበራል (የህክምናው ዘዴ)

1. ጠዋት ጥርስዎን ከመፋቅዎ በፊት 160 ሚ.ሊ. በሚይዝ ብርጭቆ አራት(4)
ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡

2. ጥርስዎን ይቦርሹ ወይም ያጽዱ ነገር ግን ለ 45 ደቂቃ ምንም ዓይነት ምግብ
ወይም ውሃ እንዳይወስዱ፡፡

3. ከ 45 ደቂቃ በኋላ ምግብ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ይችላሉ፡፡

4. ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት ከበሉ ከ 15 ደቂቃ በኋላ ለሁለት(2) ሠዓት ያክል
ምንም ዓይነት ምግብ ወይም ውሃ አይውሰዱ፡፡

5. ዕድሜያቸው የገፋና የታመሙ ሰዎች ከትንሽ ውሃ በመጀመር 4 ብርጭቆ
ውሃ ላይ እንዲደርሱ ይመከራል፡፡

6. ይህ ህክምና በህመም ላይ የሚገኙ ወይም የታመሙ ሰዎችን የመፈወስ
አቅም አለው፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እንደየበሽታዎ ለምን ያህል ቀን ህክምናውን
መውሰድ እንዳለብዎ ያሳያል፦

1. ለደም ግፊት ሰላሳ(30) ቀናት

2. ለጨጓራ ህመም አስር(10) ቀናት

3. ለስኳር ህመም ሰላሳ(30) ቀናት

4. ለሆድ ድርቀት አሥር(10) ቀናት

5. ለቲቢ ዘጠና(90) ቀናት ናቸው።

ውሃ ህይወት ነው!
ሌሎችም ያንብቡት፤ በተን በተን አድርጉት፡፡

source – Ethiotena

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here