የታይላንድ ፍርድ ቤት በገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ የ13 ሺህ 275 ዓመት የእስር ቅጣት ፈረደበት።

ፑዲት ከይቲታራደይሎክ የተባለው የ34 ዓመቱ ታይላንዳዊ ላይ የእስር ቅጣቱ የተወሰነው።

ግለሰቡ የሀገሪቱን ኢንቨስረቶች ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ስራ አለኝ በሚል ማጭበርበሩም ተነግሯል።

እንዲሁም 40 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ለኩባንያዎቹ ከ160 ሚሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲያደርጉ በማድረግ ማጭበርበሩም ተነግሯል።

ግለሰቡ በአጠቃላይ በ2 ሺህ 653 የአራጣ ማበደር እና ሌሎች የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀሎች ላይ መሳተፉም ተገልጿል።

በእነዚህ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት የቀረበው ግለሰቡ ወንጀሉን ፈፅሜያለው ብሎ በማመኑ ከተፈረደበት የእስር ቅጣት ላይ 6 ሺህ 667 ዓመት ከ6 ወር እስር ቅጣት ተቀንሶለታል ነው የተባለው።

ፍርድ ቤቱ ሁለት የፑዲት ኩባንያዎች ለተጭበረበሩ 2 ሺህ 653 ሰዎች 7 ነጥብ 5 በመቶ ዓመታዊ ወለድ አስቦላቸው ገንዘባቸውን እንዲመልስም ትእዛዝ አስተላልፏል።

የፑዲክ ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው 20 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያወጣሉ የተባለ ሲሆን፥ እንዲከፍሉ የታዘዙት የገንዘብ መጠን ደግሞ 17 ሚሊየን ዶላር ነው ተብሏል።

ፑዲት ባሳለፍነው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ ነበር በሰራው ወንጀል በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here