ዮናስ ኃይለመስቀል ኪዳኔ

በጣም በቅርቡ በአርሴናልና በኮት ዲ ቭዋር ብሄራዊ ቡድን ብዙዎችን በኳስ ሲያስደምም የኖረው ኢማኑኤል ኢቦዬ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ አስታወቀ ።

* ከባለቤቱ አውሬሊዬ ጋር በመፋታቱ በፍርድ ቤት ያለውን ንብረት ሁሉ አጥቷል

*ባንድ ወቅት በሚሊዮን ፓውንዶች በተገነቡ የቅንጦት መኖሪያ ቤቶች የተንደላቀቀው ኢቦዬ በአንዲት በጎ አሳቢ ጓደኛው ቤት መሬት ላይ ብርድልብስ አንጥፎ ይተኛል

*ልብስ ማጠብያ ማሽን መግዛት ስላልቻለና ለማሳጠብም አቅም ስለሌለው ልብሶቹን በእጆቹ ያጥባል

*ውድ መኪኖችን ባንድ ወቅት ያማርጥ የነበረው የቀድሞ ኮከብ አሁን ሰው እንዳይለየው እየተሸፋፈነ በህዝብ አውቶብስና ባቡር ይንቀሳቀሳል

*ገንዘቡ ሁሉ በቀድሞ ሚስቱ የተወሰደበት እንደሆነ፣ እርሷ የገንዘብ ወጪ ገቢውን ትቆጣጠር እንደነበር፣ እርሱ ሁሉን ለርሷ መተዉ ደካምነት እንደነበር ይናገራል

*”ምን እንደምፈርም እንኳ አላይም ነበር። ሁልጊዜ እሷ ነበረች የባንክ ዶክመንቶችን የምታስፈርመኝ። አንዴ እንዲያውም ልምምድ ላይ ሳለሁ መጥታ ልምምድ አቋርጬ ፈርሜላት አውቃለሁ። ምን ላይ እንደምፈርም ግን አስተውዬ የማላውቅ የማልረባ ሰው ነኝ”

*” አርሰናልን ለቅቄ ጋላታሳራይ ከገባሁ በኋላ እንኳ ከተከፈለኝ 8 ሚሊዮን ዩሮ 7 ሚሊየኑን ለባለቤቴና ለልጆቼ ልኬያለሁ። አሁን ግን 3 ልጆቼን እንኳ እንዳላይ ተከልክያለሁ። ከሰኔ ወር ጀምሮ አላየኋቸውም” ይላል

*ቀድሜ አብሬ የተጫወትኳቸው እነ ቴሪ ሆንሪ ዛሬም ድረስ ቲቪ ላይ ቢዝነስ ሲሰሩ ሳይ በራሴ አፍራለሁ የሚለው ኢቦዬ የማንንም እርዳታ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንና የቀድሞ ክለቡም ሆነ ሌላ ተቋም ማንኛውንም ስራ ቢሰጠው ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል።

*ከሁሉ በላይ ወጣት አፍሪካውያን ተጫዋቾች ከኔ ተማሩ፣ ዛሬ ያላችሁበትን ከፍታ ብቻ አትመልከቱ፣ እንደኔ አጉል አወዳደቅ እንዳትወድቁ ጥንቃቄ አድርጉ ሲል ይመክራል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here