የ #Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) ፌስቡክ ገጽ ቤተሰብ ያሬድ አድማሱ #Yared Admasu

ስለአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም መረጃ እና ማስረጃ ሰጠኝ፡፡

‹‹ሰሞኑን በፌስቡክ መንደር እንዲሁም በዩቲዩብ ቻናል የሚሽከረከር የድረሱልኝ የጥሪ መልእክት አለ ፡፡ …

#በታጣቂዎች_የተከበቡት_የአሰቦት_ገዳም መነኰሳት_የድረሱልን_ጥሪ_እያሰሙ_ነው፤

… የወረዳው አስተዳዳሪ “ለቃችሁ ውጡ” በማለት እገዛ ለማድረግ አልፈቀደም …

የተዋህዶ ልጆች ሼር ሼር ሼር በማድረግ ለመንግስት አካል እናድርስ … የሚለውን መረጃ እባክህን አጣራልን›› የሚል ነበር …

ከያሬድ አድማሱ ጋር ተጨማሪ  መልእክቶችን በስልክ ተለዋወጥን ስልኩን ዘጋሁ …

#አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም በፌስቡክ መንደር እንዲሁም በዩቲዩብ ቻናል የሚሽከረከር የድረሱልኝ የጥሪ መልእክት ተመልክቻለሁ – መረጃውን ብዙዎች ተቀባብለውታል፡፡

በተለይ #አሰቦት ደብረ ወገግ አቡነ ሳሙኤል ገዳም … የፌስቡክ ገጽ ዝርዝር ዘገባን ይዞ ወጥቷል፤ እንዲህ ይላል …

 • ከጥቅምት 7 ጀምሮ በየምሽቱ ከታጣቂዎቹ ጋራ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ
  ላይ ናቸው፤
 • ታጣቂዎቹ፣“የኦነግወታደሮችነን”ቢሉምተከፋይሁከተኞችሊኾኑእንደሚችሉ
  ተነግሯል፤
 • የወረዳውአስተዳደሪ፣ጥበቃእንዲያደርግላቸውበዞኑየተላለፈለትንትእዛዝ
  አልፈጸመም፤
 • በሶማሌክልልወሰንበኩልየመከላከያድጋፍቢጠየቅምየኦሮሚያመፍቀድ
  አለበት፤ተብሏል፤
 • አንዱበሌላውሲያመካኝ፣የግንቦት 1984 ዐይነቱወረራናእልቂት
  እንዳይደገም አስግቷል፤
 • በስብሰባላይያለውቅዱስሲኖዶሱ፣በአስቸኳይየኦሮሚያንክልልእገዛ
  ሊጠይቅ ይገባል፤
 • ፓትርያርኩበመክፈቻንግግርእንዳሉት፣ቤተክርስቲያንንከማዳከምስልቶች
  አንዱ ነው፡፡ … ይላል፡፡

ሌሎችም  እንዲህ …እንዲህ ተቀባብለውታል

***

አስቸኳይ መልዕክት!!
(አሰበ ተፈሪ ፣ ሐረርጌ)

የአሰቦት ገዳም መነኰሳት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ማንነታቸው በውል ያልታወቁ የታጠቁ ሐይሎች ቤተ-ክርስቲያኑን ከበዋል። የአካባቢው አስተዳደር ከፈለጋችሁ “ለቃችሁ ውጡ” በማለት እንደማይተባበር ተናግሯል።

አሰቦት ገዳም በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቀረቆረ ገዳም ነው።

ሼር በማድረግ የመንግስት አካል በቶሎ እንዲደርስላቸው እና ደህንነታቸውን እንዲጠበቅ እናድርግ!!

ለተጨማሪ መረጃ:

***

#አሰቦት

አሰቦት ገዳም ከትላንት ጀምሮ ባልታወቁ የታጠቁ ሀይሎች ተከቦ የደህንነት ስጋት እንደተጋረጠበት እየተሰማ ነዉ።

የመንግስት ፀጥታ ሀይሎች ችግር ከመፈጠሩ በፊት ወደ አከባቢዉ በፍጥነት ሊደርሱ ይገባል።

የ1984’ቱ አይነት ድራማ ድጋሚ መስተናገድ የለበትም።

***

በምዕራብ ሐረርጌ በሚኤሶ ወረዳ የሚገኘው አሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም 

ይህን ገዳም መሳለም የሚፈልግ ሐምሌ 7 ቀን በድምቀት የሚከበረውና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን የሚገኙበትን የቅድስት ሥላሴን በአልና የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ልደት ሐምሌ 10 ስለሚከበር የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ምዕመናን ከየአቅጣጫው የሚጓዙበት የጥንት ገዳም ነው፡፡

***

በፌስቡክ መንደር እንዲሁም በዩቲዩብ ቻናል የሚሽከረከር የድረሱልኝ የጥሪ መልእክት ማጣራት ጀመርኩ …

የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም  አበመኔት አባ ተክለሃይማኖት ጋር በ0924 በሚጀምረው  ስልካቸው ላይ ደወልኩ፤ አልሰራልኝም፡፡

የቀድሞ አበመኔት መምህር አባሐረገወይን ወልደሣሙኤል ጋር የእጅ ስልካቸው ላይ ደወልኩ፡፡

‹‹ሃሎው … እንደምን ከርመዋል አባታችን … ልጅዎ ጌጡ ተመስገን ነኝ – ጋዜጠኛው››

‹‹ሥላሴዎች ምስጋና ይድረሳቸው ድህና ነኝ … እንደምን ሰንብተሃል ልጄ››

/ ከሰላምት በኋላ በቀጥታ ወደ ጥያቄዬ አመራሁ/

‹‹እንዲህ ነው ነገሩ … ጥቅምት 6 ለ 7 አጥቢያ ከለሊቱ 8፡00 ሰዓት አባቶች ለጸሎት ይነሳሉ፡፡ በገዳሙ ቅጥር የማይታወቁ  ሰዎችን በመንገድ ላይ ያገኛችዋል … ፡፡ … የቤተክርስቲያኗ ደወል ይደወላል …  እነዚህ የማይታወቁ ሰዎች ወደ ጫካው ሮጠው ያመልጣሉ፡፡ …

….

እንደገና ጥቅምት 12 ቀን የአንዲት እናት ቤት በድንጋይ ተወርውሮ ይመታል! …  በገዳሙ የተከሰተው ይህ ነገር ነው፡፡ … ሰዎች ልክ እንዳንተ ደውለው ሲያወጉኝ በዚህ ገዳም እንዲህ ነገር አልተከሰተም፡፡ በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም ላይ የተነዛው ወሬ ሀሰት ነው! … ብዬ መልስ ሰጥቻችዋለሁ››

/ ከመምህር አባሐረገወይን ወልደሣሙኤል ጋር ተሰነባብተን /

***

የምዕራብ ሐረርጌ በሚኤሶ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር አላዩ አካሉ የእጅ ስልካቸው ላይ ደወልኩ

እንዲህም አሉ …

‹‹ … የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም ማንነታቸው የማይታወቁ የታጠቁ ሰዎች  አሰፈራሩን ብለው በደብዳቤ አመልክተዋል፡፡
… ጉዳዩን ለማጣራት የቀበሌ ታጣቂ ሚሊሻዎችን ልከን ነበር፡፡ ከገዳሙ ጠባቂዎች ጋር ባለመተዋወቃቸው ተደናግጠው ነበር፡፡
… ይሁንና ከገዳሙ ጠባቂዎች እንዲሁም ከአካባቢው ሚሊሻዎች በጋራ በመሆን ጥበቃ እያደረጉ ናቸው፡፡
… በፌስቡክ ላይ የተጻፉትንም በዩቱዩብ የተለቀቀውን የድረሱልን ጥሪ አይተነዋል፡፡ … ለምን አላመ እንደተፈለገ አልገባንም፡፡
… በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴና አቡነ ሣሙኤል አንድነት ገዳም ላይ የተነዛው ወሬ ሀሰት ነው!››

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here