በአዲስ አበባ 71 ሺ ኪሎ ግራም የተበላሹ እና ከባዕድ ነገሮች ጋር የተቀላቀሉ ምግብ ነክ ምርቶች፣

53 ሺ ሊትር የተበላሹ የለስላሳ ምርቶች እንዲሁም ከ2ሺ600 በላይ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድሀኒቶችን

በቁጥጥር ስር በማዋል ማስወገዱን የአዲስ አበባ ምግብ መድሀኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።

የጤና አገልግሎት ጥራትና ብቃትን ለማረጋገጥ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር

ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ መቻሉን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አለምፀሀይ ጳውሎስ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ የሚያደርገውን ክትትል እና ቁጥጥር በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ህብረተሰቡ እና

የሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ በመፍጠር በኩል የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

መንግስት በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ላይ የሚወስደው ዕርምጃ ጠንካራ እና አስተማሪ ሊሆን ይገባል ተብሏል።

ዘገባው የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here