ቱርክ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሠራተኛ በዋና ከተማዋ አንካራ ከመጠን በላይ ጠጥቶ ሲያሸከረክር በንብረትና አካል ላይ ጉዳት አደረሰ።

ከፍጠንት በላይ ሲያሸከረክር ከፊት ለፊቱ የሚሄድ መኪናን በመግጨቱ ለማምለጥ ዳግም ፍጥነት ጨምሮ ሲያሸከረክር ሌላ መኪና ላይ ጉዳት አድርሷል።

An official from the Ethiopian Embassy in Ankara, who was reportedly drunk, threatened police officers that he would “start a war” between Ethiopia and Turkey after getting involved in two traffic accidents on Nov. 26.

ፖሊሶች በቦታው ተገኝተው አደጋውን ሲመርምሩ ፍቃደኛ ባለመሆንና የአልኮል መጠጥ ምርመራ አላካሂድም በማለት ከፖሊሶች ጋር ውዝገብ ያሰነሳ ሲሆን ፖሊሶች ላይ በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል ጦርነት አሰነሳለው ሲል መዛቱን  የዓይን እማኞች ምስክርነታቸውን ለሚዲያ ሰጥተዋል፡፡

(Ortalığı birbirine kattı! ‘Türkiye ile Etiyopya arasında savaş çıkartırım’ – It’s all over the place! ‘War between Ethiopia and Turkey’)

በአደጋው አንድ ሰው ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ለአሰቸኳይ ህክምና ወደ ሆስፒታል ተወሰዷል።

የኤፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርክ ያልተገባ ባህሪ አሳይተዋል የተባሉትን የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በአስቸኳይ ወደ አገራቸው እንዲመጡ ጠርቷል።

በቱርክ አንካራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ የሚሰሩት እና ስማቸው ያልተጠቀሰው እኝህ ዲፕሎማት ባሳለፍነው እሁድ በፈፀሙት ተግባር ነው ወደ ሀገር ቤት የተጠሩት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ ዲፕሎማቱ በአፋጣኝ ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ማዘዛቸው ታውቋል።

Police officers were dispatched to the scene after the accidents as the official, whose identity remains undisclosed, reportedly refused to take an alcohol test.

After police arrived, the official reportedly vowed to “ignite a diplomatic crisis between Turkey and Ethiopia.”

One of the eyewitnesses, local man Burak Ayaydın, whose car was hit and damaged by the official, said the suspect threatened to “start a war” with Turkey.

ዲፕሎማቱ ፈፅመዋል በተባለው ያልተገባ ባህሪ ዙሪያ አስፈላጊውን ምርመራ የሚያካሂድ ኮሚቴ እንዲቋቋምም ዶክተር ወርቅነህ ማዘዛቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አግኝተናል።

እንዲህ አይነት ያልተገባ ተግባርን እንደማይታገስ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፥ ዲፕሎማቱ ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በአፋጣኝ ተገቢውን ቅጣት እንደሚያስተላልፍባቸውም አሳውቋል።

ዲፕሎማቱም አዲስ የሚዋቀረው ኮሚቴ ፊት ቀርበው ማብራሪያ እንደሚሰጡም ነው የተመለከተው።

የቱርክ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት፥ ባሳለፍነው እሁድ ምሽት ዲፕሎማቱ ሁለት የተሽከርካሪ አደጋዎችን ካደረሱ በኋላ ከቱርክ ፖሊሶች ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ ገብተዋል።

የአልኮል ምርመራ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ሲዝቱ እንደነበርም ነው መገናኛ ብዙሃኑ ያነሱት።

“This person hit another car down the road. Then he drove off and hit us … It looked like he was drunk,” Ayaydın said.

“He did not agree to take an alcohol test and called for a ‘war between Ethiopia and Turkey.’ Other people who witnessed the incident also heard him saying that,” he added.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here