በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ የሰንቀሌ የመደበኛ ስልጠና እና ፖሊስ ሙያ ኢንስቲትዩት ከ6 ሺህ በላይ ፖሊሶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ምሩቃኑ የህግ የበላይነትን እና የዜጎችን መብት በማስከበር ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ይኖራቸዋል ብለዋል።

ክልሉ ተረጋግቶ ወደ ለውጥ እንዲገባ በማድረግ ረገድ ከዚህ በፊትም የኦሮሚያ ፖሊስ ሚናው ታላቅ እንደነበረም አስታውሰዋል።

የተጀመረውን ለውጥ እንዳይደናቀፍ እና ክልሉም ሆነ ሀገሪቷን ወደ አላስፈላጊ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ ለማድረግ የፖሊስ ድርሻ ታላቅ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ከዚህ በኋላም መውደቅ አስፈላጊ ያለመሆኑን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳደሩ፥ የክልሉን ብቻ ሳይሆን፥ የሀገሪቱን ሰላም እና ጸጥታ እንዲጠበቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ኃላፊ ኮማንደር ገመቹ ጉሞሮ በበኩላቸው አዲስ ተመራቂ ፖሊሶቹ የክልሉን የጸጥታ ኃይል እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።

ተመራቂዎቹ የህግ፣ ህገ መንግስት፣ የወንጀል መከላከል እና የፖሊስ ዲሲፒሊን ስልጠና ሲቀስሙ የቆዩ መሆናውም ነው የተገለጸው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here