ረጅም የዘመን ቆይታ እየጠበቁ የሚፈጠሩ የተፈጥሮ ለውጦች የሰው ልጅን ቀልብ ይስባሉ። አንዴ ከታዩ በኋላ ተመልሰው ያንን ክስተት ለመድገም ሲመለሱ ግን እነዚህ የተፈጥሮ ለውጦች ባለፈው ካያቸው የሰው ዘርን አንዱንም ላያገኙ ይችላሉ።

ዛሬም ራሷን ቀይራ በልዩ ሁኔታ የምትሞሸረው ጨረቃ በተመሳሳይ ባለፈው ጊዜ ካያት የሰው ዘር አንዱንም ለወሬ ነጋሪ አታገኝም። ጨረቃ በእንዲህ መልኩ ራሷን ለውጣ የምትመጣበት ልዩ ክስተትን በራሷ ላይ የምትፈጥረው በ150 አመት አንዴ በመሆኑ ያኔ ካይዋት ሰዎች ውስጥ ማንን ታገኛለች? ማንም የለም።

ያኔ በሰላም ያገናኘን ብላ የተመለሰችው እ,ኤ,አ በ1868 ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ በጥቂቱ ከተከናወኑ ታላላቅ የዓለም ክስተቶች ውስጥ አንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ይጠቀሳሉ።

ጨረቃን በአዘቦት ልብሷ በምድር የኖረው ሁሉ አይቷታል። የዛሬው ግን እንደዚያ አይደለም። “Super blue blood moon” የሚል ስያሜ በተመራማሪዎች በተሰጣት የስያሜ ስሟ አምራ፣ገዝፋ እና ደምቃ የምትታየው በ150 አመት አንዴ በመሆኑ ይሄ ቀን ደግሞ ዛሬ ሆኖ በናፍቆት እየተጠበቀች ነው።

በእርግጥ ” Blue blood moon” ማለትም ጨረቃ ሙሉ ገጽታዋን ይዛና ፈክታ የምትታይበት ክስተት እኛም ብዙ ጊዜ አይተናል።

ይሄ ግን Super የሚል ማዕረግ ጨምራ ጨረቃ የምትከሰትበት ትዕይንት የተለየ ነው። አሁን ወጥተን በምሽት የምናያት መደበኛዋ ጨረቃ ካላት መጠን 30 እጥፍ ተልቃ ስትታይ፣ በ15 እጥፍ ደግሞ ብርሃኗ ይደምቃል።

የጠፈር ባለሙያዎች ቀደም ብለው እንዳስታወቁት በዚህ መልኩ የብርሃንና የመጠን ለውጥ ይዛ ከች የምትለው ጨረቃችን በሁሉም የዓለም ክፍል ትታያለች ማለት ሳይሆን፣ በውስን አካባቢዎች ብቻ መሆኑን ጠቅሰው ይህቺን በየ150 አመት አንዴ ብቻ የመጠን እና የብርሃን ለውጥ ይዛ የምትመጣዋን ልዕልት ጨረቃ የማየት ዕድሉ ያላቸው፣ በደቡብ ምዕራባዊ አሜሪካ በኩል አድርጎ፣ ፓስፊክ ውቅያኖስን ይዞ በምስራቃዊ እስያ አካባቢ ያሉ ሰዎች የዛሬዋን ደማቅና ግዙፍ ጨረቃ የሆነችውን “Super blue blood Moon” ያይዋታል ተብሏል።

የቀረነው እንግዲህ ራሳቸው ወሬውን እንደነገሩን ሁሉ፣ ራሳቸው በቴሌቭዥን መስኮት ያሳዩናል ማለት ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here