ሰባት ወረዳዎች ባሉት በዚህ ዞን የተለያዩ ሥፍራዎች ትናንት እና ከትናንት በስትያ ሰልፎች መካሄዳቸውን የዐይን እማኙ አክለው ገልጠዋል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን የወረዳ ጥያቄ ያነሳችው አዲሎ የተባለችው ቀበሌ ውስጥ ትናንት፣ ጠምባሮ በተባለችው ወረዳ ላይ ደግሞ ከትናንት በስትያ ሰልፍ ነበር ብለዋል።

ጠምባሮ ከተማ ራሱን ችሎ ጠምባሮ ከተማ አስተዳደር እንዲኾን ነዋሪው ጥያቄ ማንሳቱን የአዲሎ ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።

የትናትናውን ሰልፍ ተከትሎ አዲሎ ቀበሌ መንገዶች መዘጋታቸው እና ወደ አዲስ አበባ የሚያቀናው መንገድ አኹንም ድረስ አገልግሎት መስጠት ማቋረጡን አስረድተዋል።

ወደ አርባ ምንጭ የሚያሻግረው መንገድ በዛሬው እለት ዝግ መኾኑ ተነግሯል።

በከንባታ እና ሐዲያ ድንበር በኩል በሆሳእና በኩልም ተቃውሞ መኖሩን ነዋሪው ጠቅሰዋል።

ቅዳሜ እለት መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መኾኑንም አክለዋል።

በትናንቱም ኾነ በትናንት በስተያው ሰልፍ መንገድ ከመዝጋት ውጪ አንዳችም ግጭት አለመከሰቱን ነዋሪው ተናግረዋል።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል መንግሥት ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በሐዋሳ ከተማ ያከናወነው 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የወረዳ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢኾንም፤

ለተወሰኑ ቦታዎች ሲፈቀድ ለእነሱ ሳይፈቀድ መቅረቱ ነዋሪዎቹን ለተቃውሞ እንዳነሳሳቸው ተናግረዋል።

የምክር ቤቱ ጉባኤ ባፀደቀዉ ዉሳኔ መሠረት የኮንሶ፤ የሀላባ እና የጎፋ ሕዝቦች የሚኖሩባቸዉ አካባቢዎች በዞን አስተዳደራዊ መዋቅሮች ይደራጃሉ።

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም የሲዳማ ሕዝብን በክልል ደረጃ ለማዋቀር በቀረበው ጥያቄ ላይም በመወያየት «ተገቢነት ያለው ነው» ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here