የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ፣ በእግርዎ እየተጓዙ አሊያም ደግሞ ስራዎትን እየሰሩ በጆሮ ማዳማጫ ሙዚቃ የማድመጥ ልምዱ አለዎት? እንግዲያውስ ተከታዮቹን ነጥቦች ልብ ይበሉ፡፡

1. የመስማትና ሚዛናችንን የመጠበቅ ችግር ያስከትላል
የጆሮ ማዳመጫዎች በቀጥታ ሚዛናችንን እንዳንጠብቅ ባያደርጉም በሂደት በተለይ ሙዚቃውን ጮክ አድርገን የምንሰማ ከሆነ ግን ሚዛናችንን ለመጠበቅ በሚያስችለውና በጆሯችን ውስጠኛው ክፍል ቬስቲቡላር ሲስተም ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡

ከቤት ውጭ ስንሮጥም ሆነ ሳይክል ስንጋልብ በጆሮ ማዳመጫ ሙዚቃ የመስማት ልምዱ ካለን ለአደጋ ተጋላጭነታችንን ያሰፋዋል፡፡ በተበተለይ ደግም የትራፊክ መጨናነቅ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ለከፋ የትራፊክ አደጋ ልንጋለጥ እንችላለን፡፡

ከአደጋው ባሻገር ለረዥም ጊዜ ሙዚቃ በጆሮ ማዳመጫ የምንሰማ ከሆነ የመስማት ክህሎታችንን ልናጣ የምንችልበት አጋጣሚም ሰፊ ነው፡፡

2. በአካባቢያችን ያሉ ድምጾችን እንዳንሰማ ያደርጋል
ጆሯችንን በሙዚቃ ማዳመጫ ከዘጋን በአካባቢያችን ያሉ ድምጾችን ለመስማት እንቸገራለን፡፡ የጆሮ ማዳመጫ አድርገን በተለይ መንገድ የምናቋርጥ አሊያም ደግሞ ከእግረኞች ጋር እየተጋፋን የምንንቀሳቀስ ከሆነ ደግሞ ለአደጋ ተጋላጭነታችንን እያሰፋን መሆኑን ልብ ማለት ያሻል፡፡

የጆሮ ማዳመጫ ሳያደርጉ የመንቀሳቀስ ልምዱ ባይኖረን እንኳ በተለይ መንገድ ስናቋርጥና የተጨናነቁ መንገዶችን ስንጠቀም ድምጹን መቀነስ ተገቢ ነው፡፡

3. እንቅስቃሴን ይገታል
አጭር ገመድ ያላቸውንና የማይመቹ ማዳመጫዎችን ለመጠቀም አንገታችንን ማንጋደድ የግድ ይለናል፡፡ ይህ ደግሞ በእንቅስቃሴያችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ የጆሮ ማዳመጫ መጠቀም ግድ የሚለን ከሆነ ገመድ አልባ አሊያም ደግሞ ተመጣጣኝ ርዝመት ያላቸውን ባለገመድ ማዳመጫዎች መጠቀሙ ይመከራል፡፡

4. ትኩረት ይሰርቃል
በጆሮ ማዳመጫ ሙዚቃ እየሰማን የምንሰራ ከሆነ ትኩረታችን በሙዚቃው ይዋጥና ስራችንን በአግባቡ ለማከናወን እቸገራለን፡፡ በተለይ ደግሞ በጆሮ ማዳመጫ ሙዚቃ እየሰማን ክብደት የማንሳት አካላዊ እንቅስቃሴ ስናደርግም ሆነ ሳይክል ስንጋልብ በትኩረት ማጣት ምክንያት ለጉዳት ልንጋለጥ እንችላለን፡፡

5. ለጆሮ ኢንፌክሽን ያጋልጣል
በማሌዥያ የህክምና ሳይንስ ጆርናል የወጣ አንድ ጥናት እንዳመለከተው የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያዎች በጆሮ ጤና ላይ ችግር ይፈጥራሉ፡፡ የጆሮ ማዳመጫዎችን በምንጠቀምበት ወቅት ጆሯችን የሚያመነጨው ፈሳሽ ይጨምራል፤ ይህ ደግሞ ለባክቴርያ መራባት ምቹ በመሆኑ ለጆሮ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድላችንን ያሰፋዋል፡፡
የጆሮ ማዳመጫዎችን መጠቀም ግድ ቢለን እንኳን ንጽህናቸውን የመጠበቁ ነገር መዘንጋት አይኖርበትም፡፡

ምንጭ፡- Health24.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here