የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ በ13ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የስፖርታዊ ጨዋነት ግድፈቶች ፈጽመዋል ባላቸው አሰልጣኝና ተጫዋቾች ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳልፏል።

የዲሲፕሊን ኮሚቴ በአሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ፣ ጌታነህ ከበደ እና ኄኖክ አዱኛ ላይ ነው የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው።

የመቐለ ከተማው አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ ክለባቸው ባለፈው እሁድ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 1ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ ቡድናቸውን ከሚመሩበት ክልል ወጥተው ወደ ተጋጣሚ አሰልጣኞች በመሄድ የሲዳማ ቡናው ምክትል አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ሰድበዋል በመባሉ ነው የቅጣው ውሳኔው የተላለፈባቸው።

በጨዋታ አመራሮች በአሰልጣኙ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት በቀጣይ 5 ጨዋታዎች ቡድኑን እንዳይመሩ ቅታት ተላልፎባቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 4ሺህ ብር ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።

የደደቢቱ ጌታነህ ከበደም በተመሳሳይ የጨዋታ እና የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል።

ደደቢት በጅማ አባ ጅፋር በተሸነፈበት ጨዋታ ኄኖክ ኢሳያስን በክርኑ ተማትቶ በቀይ ካርድ ከሜዳ የወጣው ጌታነህ ከበደ የ4 ጨዋታዎች ቅታት የተጣለበት።

በተጨማሪም 4 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣትም የውሳኔው አካል ነው።

የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር ተከላካይ ሄኖክ አዱኛም ኳስ በእጁ ሆን ብሎ በእጁ በመምታቱ የጨዋታ እና የገብዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።

ሄኖክ ጅማ አባጅፋር ከደደቢት ባደረጉት ጨዋታ የተጋጣሚን ግልፅ የጎል ማስቆጠር እድል በእጁ በማውታት በማምከኑ በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ መውታቱ ይታወሳል።

ተጫዋቹ በሰራው ጥፋትም 1 ጨዋታ እና 4ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል።

ምንጭ፦ www.soccerethiopia.net

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here