ኢትዮ ቴሌኮም በ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚያስገነባው ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የስትራክቸር ስራ 58 ነጥብ 95  በመቶ መጠናቀቁን አስታወቀ።

ተቋሙ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ግንባታው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአይ.ሲ.ቲ መንደር ውስጥ የሚገነባው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ግንባታ፥ CGCOC Group በተባለው የቻይና ተቋራጭ እየተከናወነ ይገኛል።

የዋና መስሪያ ቤት ግንባታው በቀጣዩ ዓመት ህዳር ወር ላይ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ርክክብ ለማድረግ ውል እንደተያዘ ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here