ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ለመጡና በፍራንክፈርት ስታዲየም

በአገራቸው ፍቅር የወቅቱን ከፍተኛ ብርድ ተቋቁመው ለታደሙ ኢትዮጵያውያን ንግግር አደረጉ::

በንግግራቸውም:-

* “… አንድ ሆነን ለለውጥ እንነሣ፤ ዘመኑ የሚያስተኛ አይደለም፡፡

* ትናንት ከኛ ውጭ ነው፡፡

* ያለነው ዛሬ ላይ ነው፡፡

* ያልነካነው ነገ ደግሞ ከፊታችን አለ፡፡

* ተለያይተንም አንችለውም፡፡ ዛሬ ላይ ተባብረን በርትተን በሠለጠነ መንገድ በመሥራት ነገን አብረን እንገንባ፡፡

ተስፋ አደርጋለሁ፡-

* ከዐሥር ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ችግሮቿን ሁሉ ትዝታ አድርጋ የአፍሪካ ሞዴል እንደምትሆን፡፡

* ልጆቻችንም በክብር ስማችንን አንስተው ያወጋሉ፡፡

ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

* ይሄ ሁሉ ውጣ ውረድ አልፎ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በእግራችን እየተራመድን የዛሬዋን ቀን በደስታ አስታውሰን እንኳንም ለዚህች ታላቅ ሀገር ደከምን ብለን በደስታ እንደምንሞላ፡፡

ተስፋ አደርጋለሁ፡-

* ሁላችንም ወደ ልቡናችን ተመልሰን፣የትናንቱን በፍቅር ፣ በዕርቅና በይቅርታ ዘግተን፣ የነገውን አዲስ ዘመን በመደመር ፣ በአንድነትና መቻቻል በተሥፋና በፍቅር ሠርተን ለሁላችንም የምትሆን ድንቅ ሀገር እንደምንገነባ፡፡

* ልጆቻችን ወደ አውሮፓ ለትምህርት ፣ለንግድ አለዚያም ለጉብኝት እንጂ ለስደት እንደማይመጡ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አምናለሁም::”

ብለዋል::

Fitsum Arega

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here