ክቡር የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከተ.መ.ድ. የፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊ ሮዝ ሜሪ ሪካርዶ ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህም ተ.መ.ድ በአፍሪካ ቀንድ እየተካሄደ ያለውን የሰላም ጥረት እንደሚያደንቅ እና እንደሚደግፍ ተገልጿል፡፡

ሮዝ ሜሪ ባደረጉት ንግግር፣ የተመድ ዋና ጸሃፊ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሁኔታ በቅርብ እንደሚከታተሉት ገልጸው አሁን የተፈጠረው የሰላም ሁኔታ ለሌሎች አካባቢዎችም እንደምሳሌ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ ከወንዶች እኩል ማድረጉ የጾታን ተሳትፎ እና ፍትሃዊነት የሚያረጋግጥ ታላቅ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአለፉት ጥቂት ወራት ባደረገቸው ውሳኔ በአገር ውስጥም ሆነ ከጎረቤቶቿ ጋር ያለውን ለውጥ በሚመለከት አብራርተዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ተመድ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን አዲስ የሰላም፣ የትብብር እና የመነቃቃት መንፈስ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ረዳት ዋና ጸሃፊዋ፣ ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ በብቃት መወጣቷን ጠቅሰው በቀሪ ጊዜያትም ይኸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here