ይህ ህልም አይደለም? እውነት ነው ! ከትልቅ ወይም ከትንሽ መወለድ ትልቅ አያደርግም፡፡ትልቅ ህልም ይዞ መወለድ ግን ታላቅ ያደርጋል፡፡

በኔ ህይወት የመጀመሪያውን ፎቶ የተነሳሁት በተወለድኩ በ20 ቀኔ ነበር፡፡

በመቀጠል ለክርስትና በ40 ቀኔ ለጥምቀት የተነሳሁት ፎቶ ነው፡፡ሦስተኛ የተነሳሁት ፎቶ ግን የተለየ እና አንፀባራቂ ነበር፡፡

በዓለም ሕዝብ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው ይህን ክብር ለማግኘት በርካቶች ተቆጭተዋል፣ አልቅሰዋል፣ እራሳቸውን ሰውተዋል፡፡ይህ የሆነው ለዓለም ዋንጫ አሸናፊነት ነው፡፡

በ2002 ዓ.ም የሦስት ወራት ጨቅላ ሳለሁ በአፍሪካ ምድር በደቡብ አፍሪካ የሚዘጋጀውን የዓለም ዋንጫ ምክኒያት በማድረግ በሰው ዘር መገኛ በአፍሪካ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ በኮካ ኮላ አማካኝነት የዓለም ዋንጫ ታሪካዊ ጉዞ ለማድረግ እዚህ ተገኘ፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ለማግኘት እና ለመሳተፍ ሩቅ ለሆነበት ታላቅ ሕዝብ የዓለም ዋንጫ ህልም ነበር፡፡ ነገር ግን ማግኘት ባንችል እንኳን አጠገቡ ቆሞ ፎቶ ለመነሳት ግን የታደልን ነበርን፡፡

በሚኒሌየም አዳራሽ ከ5ሺ ሰው በላይ ፎቶ የተነሳ ሲሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በቤተ-መንግስት በመገኘት ልዩ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ይህ ሁሉ ሲሆን ብቸኛው የሦስት ወር ጨቅላ ህፃን በአባቴ እቅፍ ውስጥ ሆኜ ከታሪካዊው የዓለም ዋንጫ ጋር ፎቶ በመነሳት እድገቴን ጀመርኩኝ፡፡

በሦስት ዓመቴ ለእግር ኳስ ባለኝ የመጫወት ፍቅር በቀድሞ ታላቅ እግር ኳስ ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ በተመሰረተው አሴጋ ስፖርት አካዳሚ ስልጠና መውሰድ ጀመርኩኝ፡፡

አሁን የ8 ዓመቴ ላይ የምገኝ ስሆን እለት ተእለት ችሎታዬን እያሳደኩኝ እገኛለው፡፡ ትምህርቴን  በሚገባ እየተከታተልኩኝ ሲሆን በጊብሰን ስኩል ሲስተም የ3 ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡

ከአገር ውስጥ የማደንቃቸው ተጫዋቾች ውስጥ ሰለሃዲን ሰይድ፤ አዳነ ግርማ ና ጋቶች ፓኖ ሲሆኑ ከውጪ ደግሞ ሚሲ፤ ሮናልዶ፤ኔይማር፤ ጆርጅ ዊሃ ፤ መሃመድ ሳላህ ፤ እና ዋይኒሮኒ ቀልቤን ይገዙታል፡፡

እኔም ከ8 ዓመት በኋላ በ2010 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ምክኒያት በድጋሚ ታሪካዊውን የዓለም ዋንጫ በኮካ ኮላ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሲሆን ለእኔ ደግሞ ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮልኛል፡፡ ምክኒያቱም ትልቅ ተጫዋች እንድሆን  የዓለም ዋንጫ መነሳሳትን ይፈጥርልኛል፡፡

አንድ ቀን በርትቼ በመሥራት ህልሜን አሳካለው፡፡ ኮካ ኮላ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት ታዳጊዎች ከፍተኛ መነቃቃትን በመፍጠሩ ምስጋና ይገባዋል፡፡ ህልም አለኝ !ፕሮሽናል ተጫዋች ሆኜ ሀገሬን ወደታላቅ ደረጃ ለማድረስ !

አንድ ቀን!!

የካቲት 2010 ዓ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here