የክላሲን ውሃ የሚያመርተው የበላያ ኢንደስትሪያል ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣

“ንግድ ሚኒስቴር ምንም አይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጠኝ፣ እኔም ሳላውቀው ድርጅቴ መታሸጉን ቀድሞ በመገናኛ ብዙሃን ነግሮብኛል” አለ፡፡

የክላሲን ውሃ የሚያመርተው ድርጅት የሚያመርተው ውሃ ምንም የጥራት ጉድለት እንደሌለበት የሚያስረዱ እና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተረጋገጡ ሰነዶችን ለጋዜጠኞች አሳይቷል፡፡

ድርጅቱም ከነገ ጀምሮ የማሰናብታቸው ሰራተኞች እንዳሉ እወቁልኝ ብሏል፡፡

ይሄንን ወሬ እስካሰናዳንበት ድረስም የንግድ ሚኒስቴር የክላሲን ውሃ ለሚያመርተው ድርጅት ምርታችሁን ሰብስቡ የሚል ደብዳቤ እንዳልሰጠ ሰምተናል፡፡

በመገናኛ ብዙሃን፣ ምርቱ ጥራቱን ያላሟላ ነው ተብሎ ስለተወራብን ብቻ ከገበያ መውጣታችንን እወቁልን ብለዋል፡፡

ውሃ አምራች ድርጅቱም ጉዳዩን በሕግ እጠይቃለሁ ብሏል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here