የመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አስደናቂ አስተያየት

መንግስት እንደሆነ ተቀያያሪ ነው፡፡ በሊቢያ የመጨረሻው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ ጋዳፊ ሆኑ፤ የኢራቁ ደግሞ ሳዳም ሁሴን፡፡

ሶርያ የምትባለው ሀገር ለመቀጠሏ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ጎረቤቶቻችንም እየታመሱ ነው፡፡

እዚህ ሀገር እየተፈጠረ ያለው ችግርም ከነዚህ ሀገራት ባልተናነሰ አስጊ ነው፡፡ ፖለቲካዊ አመለካከትን እንደመለያያ ምክንያት ማቅረባችን ተገቢ አይደለም፡፡

የቋንቋ ልዩነታችንን፣ የኃይማኖት ልዩነታችንን በምክንያት ማቅረብ ለድክመቶቻችን ሽፋን እንደ ማበጀት ነው፡፡

4-ኪሎ ላይ #ከሐጎስ ጋር የተጣላ ሰው፤ እስከ አድዋ፣ ሽሬና አክሱም ድረስ መሳደብ፤ #ከሁሴ ጋር የተጣላ ሠው እስልምናን መስደብ ነውረኝነት ነው፡፡

በአንድ #ቶሎሳ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠር ኦሮሞን
መስደብ፣ በአንድ ሐጎስ ምክንያት ሙሉ ትግሬን መስደብ፣ በአንድ #የጎንደርተወላጅ ምክንያት ሚሊዮን ጎንደሬን መስደብ ያልተገረዘ አንደበት ውጤት ነው፡፡”
.
መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ

[ ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ ተቀንጭቦ የተወሰደ ]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here