አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ ነበሩ።

አሰልጣኝ ሥዩም በተጫዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ መድን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ካሰለጠኗቸው ቡድኖች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

አሰልጣኙ ላለፉት ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ሆስፒታሎች ከፍተኛ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ እንደነበር የሚታወስ ነው።

Kasstro Sanjaw

‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ ህይወቴ. . . ያሳደገኝ ክለቤ ነው!››  – አሰልጣኝ ስዩም አባተ

ስዩም አባተ. . . ታሞ አልጋ ላይ ሳለ ወደተኛበት ሆስፒታል አቅንቼ ሳወራው ከተናገራቸው ንግግሮች ጥቂቶቹን ላክፍላችሁ፤

‹‹ ይሔ ክለብ እኮ ዝም ብሎ ክለብ አይደለም ታሪክን አጭቆ የያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለተኛ ተጫዋቾችን ያፈራ እንደ ቅርስ ሊታይ የሚገባው ክለብ ነው፤

ሆኖም ግን ለረጅም አመታት ታሪክ የተሰራባቸውና በመስዋእትነት የተገኙ ቅርሶችን ያዘረፈው ስፖርት ኮሚሽን የእድሜ ልክ ባለ እዳ ነው፤

እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ትውልድ የለፋባቸው ዋንጫዎች የማንም ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል፤ በእለቱ አስታውሳለሁ. . .

እንደ ተራ ነገር ‹ና እና የድርሻህን ውሰድ፤› ተባልኩኝ፤ በጣም ደነገጥኩኝ፤ ምነው ቶሎ ደርሼ በነበር እና ታሪክ አቆይቼ ለክለቤ ባስረከብኩ ብዬ አሁን ድረስ እቆጫለሁ፤

ስደርስ ግን ኦና ሆኖ ነው የጠበቀኝ የጊዮርጊስ ነገር እንዲህ በመሆኑ አዝኜና አልቅሼ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ፤

ይህን አሳፋሪ ተግባር የሰሩ የወቅቱ የስፖርት ኮሚሽን ሰዎች የጊዮርጊስ እዳ አለባቸው፤ ላባችን ሜዳ ላይ ቀርቷል፤››. . . .

‹‹ የኔ ቡድን ጊዮርጊስ ከመሬት ተነስተህ ስም የምታገኝበት ቡድን አይደለም፤

ባለ ዝናና ባለታሪክ ለመሆን ብቻ ሳይሆን በስፍራህ ተመራጭ ለመሆን ጊዮርጊስ ቤት ፈተናና ስቃይ አለብህ፤

ታሪከኛ ለመሆን ዝም ብሎ የሚቻልበት ቡድን አይደለም ቡድናችን፤

ይህ ታላቅነት እየተቀጣጠለ የዘለቀው ደግሞ ከነ ይድነቃቸው ጀምሮ ነው፤

እኔ ጊዮርጊስ ቤት ተጫዋች ብቻ ሳይሆን ተማሪም ነበርኩ፤ ከነ ይድነቃቸው፣

ከነ መንግስቱ ወርቁ እየተማርኩና እውቀትን እየቀሰምኩ ነው ያደኩት፤

እነሱ የሄዱበትን መንገድ ጨዋታ አቁሜ አሰልጣኝ ስሆን ለማሰልጠን የቻልኩት ቡናን ስለሆነ እዛ ተጠቅሜበታለሁ፤

በቤቴ ያገኘሁት ትምህርት የትም ብሔድ ውጤታማ እንደሚያደርገኝ እኮ የታመነ ነው፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ለኔ አባቴ ነው፤ ታላቅ ደረገኝ፣

በእግር ኳስ አንፆ ያሳደገኝ ክለቤ ነው፤ ከአባቴ ያገኘሁት እውቀት እኮ ነው እኔንም ቡና ውስጥ አባት ያደረገኝ፤

ስለዚህም የማይካደው ሀቅ እኔ ምንም የማይቀይረኝ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍሬ – የቡና ባለውለታ ነኝ፡፡ ›› 

ያያ ዘልደታ ያሬድ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ከመሽ አረፉ

እግር ኳስ ባለወለታዋን አጣ ያውም ውብ እግር ኳስ የማራኪ ጨዋታ ባለቤት የሆነው ጋሽ ስዩም ከማንም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡና የምንግዜሙ ጀግናው ነበረ አሰልጣኝ ስዩም አባተ ነፍሱን በገነት ያኑርልን

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ አሰልጣኞች አንዱ የነበሩት አነጋፋው አሰልጣኝ ሥዩም አባተ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን “ሶከር ኢትዮጰያ” ዘገበ።

አሰልጣኝ ሥዩም በተጫዋችነት ዘመናቸው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እና ለብሔራዊ ቡድን የተጫወቱ ሲሆን ፣ካሰለጠኗቸው ክለቦች መካከል ኢትዮጵያ ቡና፣ መድን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

አሰልጣኘ ሰዩም ባደረባቸው ህመም ሳቢያ ላለፉት ወራት በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገር ሆስፒታሎች ከፍተኛ የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል ።

የሀዘን መግለጫ!!!

በአስልጣኝ ስዩም አባተ ህልፈተ ህይወት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

አሰለጣኝ ስዩም አባተ በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት የእግር ኳስ ክለብ የስራቸውን ታላላቅ ስራዎችን ማህበራችንና መላው ደጋፊ መቼም አይዘነጋውም።ስምህ ከመቃብር በላይ ጎልቶ ይነገራል።

ለመላው ቤተሰቦቹ፣ለወዳጆቹ፣ለአድናቂዎቹ በሙሉ መጽናናትን ይሰጠን ዘንድ እንመኛለን።

የአሠልጣኝ ጋሽ ስዩም አባተ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ሳሪስ በሚገኘው የፃድቅ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ (ሳሪስ አቦ) ቤተክርስቲያን
ይፈፀማል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here