ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የነበሩትን የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከሸኙ በኋላ የብሔራዊ የክብር ዘብ አባል የደንብ ልብስ ሲያስተካክሉ ታይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌሎች የአገሪቱ ላመሥልጣኖች ጋር ሆነው ወደ መኪናቸው እየተመለሱ ሳለ በድንገት ከቀይ ምንጣፍ ወጥተው የአንድ የክብር ዘበኛ አባል

የደንብ ልብስ አለባበስን ሲያስተካክሉ አብረዋቸው የነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሲደመሙ ተስተውለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሪፖርተር

የፎቶው ባለሙያ— ዳንኤል ጌታቸው

የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ የሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለት ቀናት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በዛሬው እለት ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም፥ ለጁሴፔ ኮንቴ ሽኝትት እንዳደረጉላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ተወያይተዋል።

በወቅቱም ሃገራቸው በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የፓለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችንና ለውጡን የሚመራውን መንግሥት አድንቀው ጣሊያን የለውጡን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረውን የጦርነት ሁኔታ በአዲስ የሰላምና የወዳጅነት ምዕራፍ መተካቱ በሳል እርምጃ እንደሆነም ጠቁመዋል።

በሁለትዮሸና በባለብዙ ወገን መድረኮች ሁለቱ ሀገራት ያላቸው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም በውይይታቸው ወቅት ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here