የደቡብ ፓሊስ አትሌት የሆነው በቅርቡ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና በአለም አትሌቲክስ መድረክ ስኬታማ የሆነው አትሌት ኮንስታብል ሰለሞን ባረጋ

 በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሚሊዮን ሚቲዮስ እና በክልሉ ፓሊስ ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል እጅ በክብር የኢንስፔክተርነት ማዕረግን ትናንት ምሽት በሀይሌ ሪዞርት አግኝቷል፡፡

በብራሰልሱ የዳይመንድ ሊግ ውድድር 5000 ሜትሩን በ 12 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ ከ02 ሴንቲ ሰከንድ በመጨረስ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡


የደቡብ ፖሊሱ አትሌት ከብቃቱ ባሻገር ትህትና መለያው ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ሰለሞን ባረጋ በወንዶች ዳይመንድ ሊግ ከ20 አመት በታች በ5ሺ ሜትር የአመቱን ፈጣን ሰአት አስመዝግቦ 50,000 ዶላሩን በእጁ አስገብቷል

ቴዎድሮስ ታከለ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here