አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደሀገሩ እንዲገባ ጥሪ ቀረበለት፡፡

አትሌቱ ሀገር ቤት ሲገባ የጀግና አቀባበል ለማድረግ

የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሃገሩ እንዲመለስና

ከዚህ ቀደም ለሀገሩ ያደርግ የነበረውን አስተዋጽኦ እንዲቀጥል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ አቅርበውለታል፡፡

በወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁለቱ ፌዴሬሽኖች ለአትሌት ፈይሳ የጀግና አቀባበል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እኤአ 2016 በተካሄደው የሪዮ ኦሊምፒክ ሀገሩን ወክሎ በማራቶን በተካሄደው ውድድር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡

#Ethiopia: Ethiopian Olympic Committee & Athletics Federation have called athlete #FeyisaLilesa, who protested at #RioOlympic & left Ethiopia to live in #Arizona, to return home. Both institutions said Feyisa will receive a hero’s welcome had he chose to return.

Source: Aweke Abreham

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here