የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ በዝምቧብዌ በሚካሄደው ምርጫ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ።

የዝንቧብዌ መንግስት ከጥቂት ወራት በፊት ዘንድሮ የሚካሔደውን ምርጫ እንዲታዘቡ

የአውሮፓና የአፍሪካ ሕህረትን ጨምሮ የመንግስታቱ ድርጅትን የልኡካን ቡድን እንዲታዘቡ ጋብዘው ነበር።

በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ሁለት ቡድን ያለው የታዛቢዎች አካላት የአገሪቱን ምርጫ እንዲታዘብ የወሰነ ሲሆን፥

አንዱን ቡድን የመምራት ስራ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ ሕብረቱ መመረጣቸው ተገልጿል።

ህብረቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምርጫውን የሚታዘበውን የልዑካን ቡድን እንዲመሩ ያደረጉት በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በነበራቸው ተሳትፎ ነው።

አቶ ኃይለማርያም በዚሁ መሰረትም ከ10 ቀን በኋላ ወደ ሀረሬ እንደሚያመሩም ተጠቁሟል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገራታቸው ብሎም በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የዴሞክራሲ ስርአትን ለመገንባትና

በተለያዩ አለማቀፍና አሕጉር አቀፍ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ባደረጉት ተሳትፎ እንደተመረጡ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥም አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ፣የኔፓድና የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል።

Former Prime Minister Hailemariam Desalegn has been appointed to chair an election observation mission to Zimbabwe.

Moussa Faqi, chairman of the African Union (AU) has selected Ethiopia’s former Prime Minister to lead the AU Election Observation Mission (AU-EOM) which will be conducted on July 30, 2018.

ምንጭ፦ ኢዜአ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here