ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈት 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ተደራጅታ ኢትዮጵያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወረረች፡፡

ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር በፅናት ተዋጋች፡፡

ምንም እንኳን የጠላት ጦር ሃያል ቢሆንም፤ አርበኞች ግን ከቀን ወደ ቀን ድል እየተቀዳጁ የጣሊያን ወታደሮችን መፈናፈኛና መግቢያ መውጫ አሳጧቸው፡፡

ከጣሊያን ወታደሮች ይማርኳቸው በነበሩ መሣሪያዎች ራሳቸውን እያደራጁ አብዛኛውን የገጠር ክፍል ተቆጣጠሩ፡፡

ከብዙ ትግል በኋላ የኢትዮጵያ አርበኞች በጣሊያን ወታደሮች ላይ ጥቃታቸውን አፋፋሙ፡፡

ጣሊያኖች ክፉኛ ተሸነፉ፡፡ በየቦታው ድል የመሆናቸው ዜና ተነገረ፤_በዘመቻውም ጣሊያኖች አዲስ አበባን ለቅቀው ፈረጠጡ፡፡

ንጉሰ ነገስቱም ሚያዝያ 27 በአዲስ አበባ ታላቁ ቤተ-መንግሥት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለቡ፡፡

በአርበኞች ታላቅ ተጋድሎ፤ ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በልጆቿ መስዋዕትነትና የደም ማኅተም ነፃነቷን አፀናች፡፡

አካኪ_ዘራፍ_አካኪ_ዘራፍ፤

ጭው_ሲል_ገዳይ_ደጀን_ሲላላ፣ 
የጠቅል_አሽከር_የጠቅል_ባላ።

ጎራዴ_መዞ_ሲሄድ_ከቤቱ፣ 
ወየው_ሰው_ፈጀ_አለች_እናቱ፡፡

እንኳን_እናቱ_የወለደችው፤ 
ኮራች_አማቱ_የተጋባችው፡፡

በሰፊ_አውድማ_የተበጠረው፤ 
ገለባው_ሄዶ_ምርቱ_የቀረው፡፡ 
ዘራፍ_ሰው_በሰው፣ 
በደረሰበት_ባፎቄ_እሚያርሰው።

ሰንደቅ_አላማ_ኮከብ_ሲመስል፣ 
ነጋሪት_አብጅር_አብጅር_ሲል፣ 
መትረየስ_ሲጮህ_መድፉ_ሲያጓራ፣ 
ደጀን_ሲበተን_እርሳስ_ሲዘራ፣ 
አጣድፎ_ገዳይ_በያዘው_ጣምራ፤ 
ባባቱ_ወጥቷል_ልጁም_አይፈራ፤ 
አንድ_ለናቱ_የሜዳ_ጎራ፡፡ ……

እንዲህ ባለ ፉከራ ነበር አገርን ለማስከበር ሲሉ ጀግኖች አርበኞች በጦር ግንባር ላይ ያለ ፍርሃትና ስጋት ጠላታቸውን በጎራዴ ያጠቁት፡፡

ደፋርነትና ቆራጥነት በልበ ሙሉ የወኔ ጀግንነት በኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ቀርጸው ለራሳቸው ሳይኖሩ ስለኛ ኖረው ለአገራችን ክብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው ኢትዮጵያን ያቆዩልን፡፡

እኛስ የዚህ ዘመን ትውልድ አባል የሆነው የአገር አሻራችን በምን ይታወስ?

እንደ ቀድሞዎቹ አገርን ከወራሪ ጦር በመከላከል ?

ወይስ አፈሙዙን የሰበቀብንን ድህነትን በመዋጋት? ወይስ የባህር ማዶ ፋሽን ተከታይ ወይስ እጅና እግራችንን አጣጥፈን በመቀመጥ የአገርና የቤተሰብ ሸክም በመሆን?

ንገሩኝ እስኪ የኛስ የድል ብስራት ምን ይሁን?

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here